2009-09-11 11:35:39

የብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ደምረው: የኢትዮጵያና የኤርትራ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበርና የአዲስ አበባ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ የአዲስ ዓመት መልእክትና ቃለ ቡራኬ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“የምሕረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለህ፣ ምድረበዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ፣ የምድረበዳ ተራሮች ይረካሉ” (መዝ. 64፣11-12)

ክቡራን ምእመናን፣ በሩቅና ብቅርብ ያላችሁ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፣ ክቡራን የቤተ አገልጋዮችና በጎ ፈቃድ ያላችሁ ሰዎች በሙሉ፤ እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ።

የዘመን መለወጫ በዓል ቀደም ብሎ ለነበሩት ሰዎች እንደነበረ ሁሉ፣ ለዛሬው ትውልድም ቀጣይ ሆኖ ለ2002 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ በዓል፣ እግዚአብሔር ጠብቆን በሰላም ስለአደረሰን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንና በራሴ ስም እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.