2009-09-11 13:20:25

ዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ቅነሳ ማረጋገጥ እና ብሎም ማምከን


ትላንትና በሜክሲኮ ርእሰ ከተማ የተካሄደው 62ኛው የተባበሩት መንሥግታት የማኅበራዊ አገልግሎት፣ የመገናኛ እና የማስታወቂያ ጽ/ቤት ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑት የድጋፍ እና የትብብር የህንጸት እና የልማት ድጋፍ RealAudioMP3 ማኅበራት በጋራ ያካሄደው ስብሰባ በንግግር የከፈቱት የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ዓለማችን ከጦር መሣሪያ ምርት እና ከተራ እና ከተራቀቀው የጦር መሣሪያ ሽቅድድም ነጻ ይሆን ዘንድ ጥሪ በማቅረብ ዓለም አቀፋዊ የትጥቅ መፍታት ዓላማ ግቡን እንዲመታ ደጋግመው በማሳሰብ፣ በአለም አንጻር ሲታይ ለጦር መሣሪያ ንግድ እና ምርት የሚፈሳው መዋዕለ ንዋይ ሺሕ ሚሊያርድ ዶላር መሆኑ እና በዚህ ሳይገታ ከእለት ወደ እለት ከፍ እያለ መሆኑ አብራርተዋል። በዚህ “ለሰላም እና ለእድገት፣ ባስቸኳይ ትጥቅ መፍታት” በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ስብሰባ ከ70 የተለያዩ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑት የድጋፍ እና የትብብር ማኅበራት የተወጣጡ 1700 ተወካዮች መሳተፋቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ባን ኪ ሙን ባሰሙት ንግግር ቀዝቃዛው ጦርነት አክትሞለት ያለም ህዝብ የጦር መሳሪያ ቅነሳ እና ብሎም ለዓለም አቀፍ ትጥቅ መፍታት መሠረት ይሆናል ያለው ተስፋው እየጨለመ የጦር መሣሪያ ምርት እና ሽቅድድም ከፍ እያለ ለሰው ዘር በጠቅላላ የሕይወት ኅልውና እጅግ ለአደጋ እያጋለጠ ነው ካሉ በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ 20 ሺህ የኑክሊያር ጦር መሣሪያ እንዳለ ገልጠው፣ የጦር መሣሪያ ቅነሳ እና ጨርሶ እንዲወገድ በሚደረገው ዘመቻ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ በማመስገን ዓላማው ግቡን እንዲመታ በሚደረገው ጥረት መቼም እንዳይዝሉ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.