2009-09-11 13:12:13

በጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ለተጎዱት ድጋፍ እና ትብብር


ባለፉት ቀናት የአፍሪካ ምዕራባዊ ክልል እጅግ ባጠቃው ኃይለኛ ዝናብ ሳቢያ በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ በቡርኪናፋሶ የጉዳቱ መጠን RealAudioMP3 እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል። በዚህ የቡርኪናፋሶ ርእሰ ከተማን እጅግ ያጠቃው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ለተጎዳው ሕዝብ ከአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አቢይ ትብብር እና ድጋፍ እየቀረበ መሆኑ ተገልጠዋል።

የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኩፐላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ሰራፊን ፍራንስዋ ሩዋምባ የአገሪቱ ሕዝብ በዚህ የትብብር እና የድጋፍ እቅድ ቀዳሚ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል። በአደጋው ሳቢያ ለተጎዳው ህዝብ መሠረታዊው ድጋፍ ለማቅረብ 1.5 ሚሊዮን ኤውሮ እንደሚያስፈልግ ያገሪቱ ርእሰ ብሔር ብላይር ኮፓኦረ አስታውቀዋል።

የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት የትብብር እና የድጋፍ ጥሪ፣ የሰራሊዮን ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከተጎዳው ሕዝብ ጎን በመሆን መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ እንደምታቀርብ አረጋግጠዋል። ቤተ ክርስትያን እያቀረበቸው ባለው ድጋፍ ቁምስናዎች የካቶሊክ የእርዳታ እና የትብብር ማኅበራት ካሪታስ በመባል የሚጠራው የካቶልክ ቤተ ክርስያን የእርዳታ ድርጅት ሰራሊዮን በሚግኘው ቅርንጫፉ እየተሳተፉ መሆናቸውም ታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.