2009-09-11 13:08:24

በሰራሊዮን የጣለው ኃይለኛ ዝናብ እና ያስከተለው አደጋ


ባለፈው ማክሰኞ ከሰራሊዮን ርእሰ ከተማ ፍሪታውን በስተ ምስራ ቅ በሚገኘው ቶምቦ ክልል አቀራቢያ ባለው ወንዝ አንዲት 241 መንገደኞች አሳፍራ ትጓዝ የነበረቸው መርከብ ይዘንብ በነበረው ኃይለኛ ዝናብ RealAudioMP3 እና በወረደው መብረቅ ሳቢያ በደረሰባት አደጋ መስመጧ ሲነገር፣ ከተሳፋሩት ውስጥ 200 ሰዎች ገና አለ መገኘታቸው ከሰራሊዮን የሚተላለፉ ዜናዎች ይጠቁማሉ። የአገሪቱ መንግሥት ምንጮች እንደሚሉትም ከሆነ የተሳፋሪው ብዛት 300 ሳይሆኑ እንደማይቀር ለማወቅ ሲቻል፣ የፍሪታውን የማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒ. መሥሪያ ቤት ቅርንጫፍ ተጠሪ ከቢቢሲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአደጋ ወቅት ተሳፋሪው ህዝብ ለህይወት ዋስት እና ደህንነት ሊጠቀምበት የሚችል ምንም አይነት የሕይወት አድን መሣሪያ እንዳልነበረም አስታውቀዋል።

ገና በመፈለግ ላይ ካሉት ውስጥ በብዛት ሕፃናት መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የ 12 ሰዎች ሬሳ መገኘኙ እና 40 የባህር አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት አማካኝነት ከሞት አደጋ መትረፋቸው የማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒ. ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት በመግለጥ፣ ኃይለኛው ዝናብ አሁንም ገና እየቀጠለ በመሆኑ የባህር አደጋ የመከላከያ ኃይል ለሚሰጡት አስቸኳይ እርዳታ አቢይ መሰናክል መሆኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.