2009-09-09 14:14:24

ቅሌት እና ሙስና ኢሞራላዊ ድርጊቶችን በጽናት ለመዋጋት


የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ካሪታስ ኢንተናሺናሊስ በመባል የሚጠራው ዓለም አቀፍ የተራድኦ ማኅበር ካለማችን ቅሌት እና ሙስና ለማጥፋት በጠቅላላ ኢሞራዊ ተግባሮችን በጋራ ለመዋጋት የሚጠይቅ RealAudioMP3 50 የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች የተለያዩ የተራድኦ ማህበራት ሊቀ መናብርት እንዲሁም የተለያዩ የሰብአዊ እና የግብረ ሰናይ ማኅበራት በጋራ የፈረሙበት ሞራላዊ ጥያቄ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ማስተላለፋቸው ተገለጠ።

ይኸንን ለተለያዩ ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ እና ብሎም ሰብአዊ ችግር የሚያጋልጠው ኢሞራላዊ ድርጊት ለመዋጋት እና ብሎም ለማጥፋት ሁሉም ካለ መታከት በተሰጠው ኃላፊነት አቢይ አስተዋጽኦ ያበርክት ዘንድ የሚጠይቀው መግለጫ ለመልካም እድል እና ለተስፋ በር መሆኑ በማመን የተላለፈ ሲሆን፣ በተጨማሪም ባለማችን ተከስቶ ያለው ማኅብራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ ለያይ አጥር ለማስወገድ የሚያግዝ መሆኑ የተላለፈው መልእክት የፈረሙበት አካላት ያስገነዝባሉ።

ግብረ ገባዊ ሕይወት ለማረጋገጥ ሥር ነቀላዊ ለውጥ እንደሚያስፈልግ የገለጠው መልእክት፣ ቅንነት ሰብአዊ ምሉእነት የተሰኙትን ግብረ ገባዊ እሰይቶች ቅሌትን እና ሙስናን የመሳሰሉት ግድፈቶችን ለመዋጋት ብሎም ለማጥፋት የሚያነቃቁ እና የሚደግፉ መሠረታዊ የግብረ ገባዊ ሕይወት ተግባሮች ወሳኝ መሆናቸው ያብራራው መልእክት፣ በፖለቲካው በማኅበራዊው እና በኤኮኖሚያዊው ዘርፍ የሚካሄደው ሥራ ግልጽነት እንደሚያሻው እና ይህ ደግሞ ታማኝነትን ለማረጋገጥ ለሚደግፍ ለተኃድሶ እና ለክለሳ ሂደት ወሳኝ መሆኑም ተምልክቶበት ይገኛል። ቅሌት እና ሙስና ድኽነትን እንደሚያባብስ የጠቀሰው የካሪታስ ኢንተርናዞዮናሊስ መልእክት አክሎ እ.ኤ.አ. በ 2003 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ቅሌት እና ሙስናን የመሳሰሉት ክስተቶችን ካለማችን ገጽ ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት የሚያስተባበር ዓለም አቀፍ ውሳኔ በመጥቀስ ሁሉም ይኸንን የመልካም እድል እና የተስፋ በር ከፋች የሆነው ሥነ ምግባር ማረጋገጥ ለዓለማችን ሰላም መሠረት እንደሚሆንም የካሪታስ ኢንተርናሺናሊስ መልእክት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.