2009-09-09 14:18:09

መንፈሳዊ ድጋፍ ለቀድሞ የታሚል ታይገርስ ተዋጊ ኃይል አባላት


የስሪ ላንካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የቀድሞ የታሚል ታይገርስ ተዋጊ ኃይል አባላት ከስሪ ላንካ ኅብረተሰብ ጋር በሰላም እና በተሟላ እርቅ ተዋህደው ለመኖር እንዲችሉ መንፈሳዊ ድጋፍ ለማቅረብ ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጠ። RealAudioMP3 የማናር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ራያፑ ጆሴፍ ይኸንን ጉዳይ በተመለከተ በክልሉ ከሚገኘው የመከላከያ ህይል አባላት ዋና አዛዥ ጀነራል ካማል ጉናራተ ጋር ተገናኝተው እንደተወያዩ ከስሪ ላንካ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተላለፈ ዜና ይጠቁማል።

እነዚህ የቀድም የታሚል ነጻ አውጪ ግንባር አባላት ከሲሪላካ ኅብረትሰብ ጋር በሰላም ተዋህደው እንዲኖሩ መንግሥት እያካሄደው ያለው የተሃድሶ እና የማረሚያ ድጋፍ ለውህደቱ እና ለማህበራዊው ሰላም ለብቻው ወሳኝ እንዳልሆነ ብፁዕ አቡነ ራያፑ ጆሴፍ ገልጠው፣ መንፈሳዊ ድጋፍ እና ሕንጸት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

አንድ ሰው የተሟላ እድገት እንዲጎናጸፍ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ሕንጸት እንደሚያስፈልገው የተረጋገጠ መሆኑ የስሪ ላንካ ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ በማብራራት፣ የቀድሞ ነጻ አውጪ ኃይል አባላት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ያሳለፉት እና የነበሩበትን ሕይወት እግምት ውስጥ በማስገባት ያለባቸው ስነ አእምሮአዊ ሰብአዊ ማኅብራዊ ድንጋጤ ነቅሎ ለአንድ አዲስ ሕይወት ለማዘጋጀት የፖሊቲካ ማረሚያ እና የተኃድሶ መርሃ ግብር ለብቻው ዋስትና እንደሌለው ያብራራው የብፁዓን ጳጳሳት ጥያቄ፣ መንፈሳዊ ሕንጸት አስፈላጊ ነው እንዳለም ኡካኔውስ የተሰኘው የዜና አገልግሎት ያሰራጨው የዜና ምንጭ ይጠቁማል።

ይህ በንዲህ እንዳለም የዜና አገልግሎቱ እንዳመለከተውም መንግሥት ባቋቋመው የጸባይ ማረሚያ እና የማገገሚያ ማእከል 300 ሺሕ የቀድሞ የታይገር ታሚሊስ ነጻ አውጪ ግንባር አባላት እንድሚገኙም ታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.