2009-09-09 14:15:58

መሃይምነትን በመዋጋት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ማነቃቃት


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን አለም አቀፍ የጸረ ማሃይምነት ቀን ምክንያት በማድረግ ትላትና ባስተላለፉት መልእክት ላቅመ አዳም የደረሱ በጠቅላላ 776 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ገና ፊደል ያልቆጠረ RealAudioMP3 ፣ እንዲሁም 75 ሚሊዮን ሕጻናት ትምህርት የማግኘት እድል እና መብት የተነፈጋቸው መሆኑ በማመልከት፣ ሁሉም ይኸንን የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በሁሉም አገሮች እንዳይነቃቃ እንቅፋት የሆነው አንገብጋቢው ችግር መዋጋት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

መሃይምነትን ከዓለማችን ገድ ጨርሶ ለማጥፋት በዚሁ ዘርፍ አቢይ ሚና የሚጫወተው ትምህርት ለሁልም የተሰኘውን ዓላማ የያነገበው የግብረ ሠናይ ማህበር ሊቀ መንበር አና ማሪያ ኤረራ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በፖለቲካ በማህበራዊ በባህላዊ እና በኤኮኖሚያዊ ምክንያት ብዙ ሕዝብ ከሚኖርበት ማኅበርሰብ ጋር ሳይቀላቀል ተነጥሎ ከመማር መብት ተገሎ አለ ምንም ትምህርት የማግኘት እድል እንደሚኖር ጠቅሰው መሃይምነት ጸረ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ነው ብለዋል።

የትምህርት እድል እና ሕንጸት ተያይዘው የሚሄዱ ለሰብአዊ ሙሉአዊ እድገት ወሳኝ መሆናቸው ገልጠው፣ በብዙ አገሮች ትምህርት የማግኘት እድል ከፍ ያለ ሆኖ ሲገኝ ሕንጸት ጎድሎ ይታያል፣ ሕንጸት አለ የትምህርት እድል ለብቻው ሙሉአዊ እድገት እንደማያጎናጽፍም አብራርተው፣ የሰው ልጅ የሚሰማውን የሚያየውን የሚባለውን ሁሉ ገምግሞ ገንቢ ትችት እና ሂስ የማቅረብ ብቃቱ እንዲያጎለብት ትምህርት እና ሕንጸት ያስፈልገዋል። እያንዳንዱ የሰው ልጅ የተሰጠው የነጻነት ጸጋ የሚኖረው እና የሚያጎለብተው ትምህርት ሲያገኝ ብቻ ነው ብለው ስለዚህ አለ መማር ጸረ ነጻነት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.