2009-09-07 15:28:44

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መልእክት ከቪተርቦ.


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ትናትና ሰንበት መስከረም ስድስት ቀን ሮማ ከተማ አቅራብያ በምትገኘው ቪተርቦ ከተማ ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስድስትገኛ ቬተርቦ ከተማ ሲደርሱ እና ሲነሱ በከተማይቱ እና በየአከባቢው ህዝብ ደማቅ አቀባበል እና አሽናኘት ተደርጎላቸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በፖላንድ የክራኾቭያ ሀገረ ስብከት እና በሮማ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ በጋርዮሽ ያዘጋጁት ፡ ሰዎች እና ሃይማኖቶች የተሰየመ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለዚሁ ስብሰባ ደማቅ ሰላምታ የበርቱ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል።

በፖላንድ የክራኾቭያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ስታንስላው ድቪጽ ከስብሰባው በፊት መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ስብሰባውን በንግግር መክፈታቸው መገናኘ ብዙኀን አመልክተዋል።

ሌላ ስብሰባው ከሚካሄድበት ቦታ የደረሰ ዜና እንደገለጠው ፡ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮች የሀገሪቱ የቤተክህነት አባላት እና የመንግስት ባለስልጣናት በዚሁ ስብሰባ ተሳታፊ ሁነዋል ።

ስብሰባው የጸሎት እና እኤአ ብ1986 ጣልያን ላይ አሲሲ ውስጥ የተካሄደው የተለያዩ የሃይማኖት አበው ስለ ሰላም ያካሄዱት ዓቢይ ስብሰባ ቀጣይ መሆኑ ተገልጠዋል ።

የክራኾቭያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ስታንስላው ዲቪጽ እና የሮማንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ሰራፊም በጋራ ስለሰላም የቅዳሴ ሥርዓት እንማ ጸሎት መፈጸናቸው ከቦታው የድጸረሰ ዜና አስገንዝበዋል ።

የዓለም ጦርነቶች በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ሕይወት ከመቅጠፋቸው እና ንብረት ከማውደማቸው በኃላ ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ሰላም ችሮ የኤውሮጳ ሕብረት እስከ መቆርቆር መድረሳችን ክብርና ምስጋና ይድረሰው ማለታቸው ዜናው ለጥቆ ገልጠዋል ።

የነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የግል ጸሐፊ የነበሩ እና በፖላንድ የክራኾቭያ ሊቀጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ስታንስላው ዲቪጽ ሰላም አንዴ ተገኝቶ ዘላቂ ሆኖ የሚኖር ሳይሆን እንክብካቤ የሚያሻው መሆኑ ማመልከታቸው ተያይዞ ተገልጠዋል።

ህልም ያለ ዓለማውነት ግድ የለሽነት እና መጠን የሌለው ፍጆታ የሰላም ተጻራሪ መሆናቸው ብፅዕነታቸው መግለጻቸውም ተነግረዋል።

የሮማንያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ሰራፊም በበኩላቸው ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ከተካሄደበት ሰባ ዓመት በኃላ እና ኮሚኒስም ካከተመ ሃያ ዓመታት በኃላ ፡ የናዚ ጀርመን ዓመጽ ከተፈጸመባት ክራኾቪያ ከተማ እግዚአብሔር ለዓለም ህዝቦች ሰላም ስለቻረልን የሃይማኖት አበው እነሆ በጋራ እናመሰግኖዋላን ሲሉ በስብሰባው ለተገኙ መግለጣቸው ተመልክተዋል።የዚሁ ስብሰባ ተሳታፊዎች ይሁዲዎች በናዚ ጀርመን ወደ ለቁበት አውስሽቪትጽ በመጓዝ የጸሎት ሥርዓት እንደሚፈጽሙ ተነግረዋል።

በዚሁ በፖላንድ የክራኾቭያ ሀገረ ስብከት እና በሮማ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ ያዘጋጁት የተለያዩ ሃይማኖቶች የጸሎት ስብስብ የክርስትያን የአይሁድ ኢስላም እና ቡድሃ ሃይማኖቶች ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸው ከክራኾቭያ የመጣ ዜና አገንዝበዋል ። ስብሰባው በጸሎት እና አስተንትኖ ተወስኖ ሳይቀር የዓለም ፖሊትካዊ እና ኤኮኖምያዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተም እየተወያየ መሆኑ አብሮ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል ። የክራኾቭያ የሃይማኖቶች አበው ስብሰባ ከሁለት ቀናት በኃላ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.