2009-09-07 14:36:17

ኬኒያ


በኬኒያ ባለፈው ወር የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ሂላርይ ክሊንተን ይፋዊ ጉብኝት እያካሄዱ በነበሩበት ወቅት የተለያዩ የሽበራ ጥቃት ለመጣል በመዘጋጅት ላይ ነበሩ የተባሉት አክራሪያን ሙስሊሞች RealAudioMP3 የኬኒያ የጽጥታ እና የደህንነት አባላት ባደረጉት ክትትል መሠረት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የኪኒያው ሳንዳይ ኔሽን የተሰኘው ዕለታዊ ጋዜጣ የኬኒያ የሰለላ ድርጅት ምንጭ በመጠቀስ ካሰራጨው ዜና ለመወቅ ተችለዋል።

ያሸባሪያኑ አንዱ ኢላማ ዋና ጸሓፊ ሂላርይ ክሊንተን አርፈውበት የነበረው እንግዳ ማረፊያ ቤት አቅራቢያ እንደነበርም ጋዜጣው ያመለክታል፣ ሊጣል ታስቦ የነበረው የሽበራው ጥቃት ጠንሳሽ በሶማሊያ ያልቃይዳ የቀኝ እጅ የሚባለው የአል ሳባብ አባላት መሆናቸው እና በድርጊቱ አምስት ሰዎች ከነርሱም ውስጥ እንዲት ሴት ጭምሮ ሁለት የዴን ማርክ ፓስፖርት ያላቸው መሆናቸውም ጋዜጣው ዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.