2009-09-07 14:29:27

አፍጋኒስታን


ባለፈው ዓርብ በአፍጋኒታን ኢሳፍ በመባል የሚጠራው በኔቶ የሰሜን ቃል ኪዳን የመከላከያ ኋይል የሚመራው የሰላም አስከባሪ ኃይል በኩንዳዝ አወራጃ በአየር ኃይል ተሸኝቶ የሰነዘረው ጥቃት አንድ ሕጻን RealAudioMP3 እና ስድስት ሰላማውያን ሰዎች የሚገኙባቸው በጠቅላላ 54 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው የኩንዳዝ አውራጃ አስተዳዳሪ ሞሃማድ ኦማር አስታውቀዋል።

ዋሽንግቶን ፖስት የተሰኘው የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዕለታዊ ጋዜጣ የኔቶ የጉዳዩ አጣሪ ድርገት የሰጠው መግለጫ ነው ብሎ ካሰራጨው ዜና፣ ለሞት የተዳረጉት 20 ሰላማውያን ሰዎች የሚገኙባቸው 125 ሰዎች መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። ሌላው ፓህጅዊክ የተሰኘው የአፍጋኒስታን የዜና ምንጭ የክልሉ ነዋሪው ህዝብ ጠቅሶ 150 ለሞት መዳረጋቸው ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.