2009-09-07 14:27:53

ብሔራዊው የዓለማውያን ምእመናን ጉባኤ በናይሮቢ


በኬኒያ ርእሰ ከተማ የአገሪቱ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጥሪ መሠረት እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 18 ቀን እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. እናንተ የምድር ጨው ናችሁ … የዓለም ብርሃን ናችሁ የሚለው በማቲዮስ ወንጌል ያለው ክርስቶሳዊ ቃል RealAudioMP3 መርህ ያደረገ እንዲሁም እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በሮማ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የአፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ልዩ ሁለተኛው የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በማተኮርም ጭምር መካሄዱ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

ይህ የዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተግባር እና የኬኒያው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዓለማውያን ምእመናን እና የቤተሰብ ሃዋርያዊ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ያዘጋጀው ጉባኤ እንደነበረም ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። ጉባኤ ከኬኒያ 15 ሰበካዎች ከአራት ሜትሮፖሊ ከተለያዩ የካቶሊክ የዓለማውያን ምእመናን ማኅበራት እና እንቅስቃሴዎች አባላት የተወጣጡ በጠቅላላ 70 ልኡካን ማሳተፉ ዜኒት የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.