2009-09-07 14:19:36

ቤተሰብ የመጪው ብሩህ ተስፋ ነው


ባለፈው ዓርብ ፖምፐይ ወደ ሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ብሔራዊ የቤተሰብ ለቤተሰብ መንፈሳዊ ንግደት መከናወኑ ተገለጠ። በዚህ የኢጣሊያው የመጪው ብሩህ ተስፋ በቤተሰብ ላይ የተመሠረተ ነው RealAudioMP3 በሚል መርህ ቃል የተካሄደው መንፈሳዊ ንግደ አስመልከተው የኢጣሊያ የተሃድሶ ማህበር ሊቀ መንበር ሳልቫቶረ ማርቲነዝ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ተሳታፊው ህዝብ 10 ሺህ እንደነበረ ጠቅሰው፣ በዚህ መንፈሳዊ እሰይታ መቃወስ በስፋት በሚታይበት ኅብረሰብ፣ መፍትሔው በማርያም አማላጅነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እና መመለስ መሆኑ የመሰከረ መንፈሳዊ መርሃ ግብር ነበር ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መፍነሳዊ ንግደቱን ላዘጋጁት እና ለተሳታፊዎች ቡራኬአቸውን በማስተላለፍ፣ ተሳታፊዎችን ሁሉ ባባታዊ ፍቅራቸው ምስጋናን እንዳስተላለፉ ማርቲነዝ ገልጠው፣ ቅዱስነታቸው ፍቅር በሐቅ በተሰኘው አዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት እምነታችን ሕይወታችን የምንመራበት አድማስ በማብራራት በዚህ በምንኖርበት ዘመን ለሚደረገው የእድገት ሂደት ክርስትናና ክርስትያኖች እንደሚያስፈልጉት አስረድተዋል። በችግር ላይ ለሚገኙት ቤተሰቦች በመንፈሳዊው በማህበራዊው እና በግብረ ሰናይ ድጋፍ ማቅረብ የሁሉም ክርስትያን ኃላፊነት መሆኑ በማመን በዚህ በተካሄደው መንፈሳዊ ንግደት የተሳተፉት ሁሉም ይኸንን የቅድሱ አብታችን መሪ ትምህርት ያጎላ እና የመሰከረ መሆኑ ለማረጋገጥ እንደቻሉ ገልጠዋል። በመጨረሻውም በዓለማችን ባካባቢያችን የሚታየውን የፍቅር መቃውስ እና ለፍቅር የሚሰጠው የተሳሳተው ትርጉም፣ ቤተሰብ ፍቅርን በማደስ፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸው ኃላፊነት እና በፍቅር በማነጽ ቤተሰብን የሚያድን ቤተክስርስትያንን እንደሚያድን እና ብሎም ኅብረሰብን እንደሚያድን የማያጠራጥረው እማኝነት የጎላበት መንፈሳዊ መርሃ ግብር ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.