2009-09-07 14:25:50

ሰዎች እና ሃይማኖት


የኢጣሊያ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር እስከ መሰከረም 8 ቀን 2009 ዓ.ም. “ሰዎች እና ሃይማኖቶ’ በሚል ርእስ ሥር በክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የጠራው ጉባኤ ትላትና በክራኮቪያ ከተማ የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ድስዝዊች በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ መጀመሩ ተገለጠ። ይህ በዚህ የኢጣሊያው የካቶሊክ ማህበር እና የክራኮቪያ ሰበካ በጋራ ያዘጋጁት ጉባኤ የአሲሲ መንፈስ በክራኮቪያ በሚል ርእስ ሥር እርሱም ሁሉም ሃይማኖቶች በመገናኘት በጋራ ለሰላም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ጠለቅ በማድረግ በተወያየው ስብሰባ በማስጀመር በጉባኤው ከፖለቲካው ዓለም የታሪክ የኤኮኖሚ የፖሊቲካ ሊቃውንት እና እንዲሁም ያአይሁድ የእስላም እና የሌሎች ክርስትያን ኣቢያተ ክርስትያን ልኡካን እየተሳተፉ መሆናቸው ተገልጠዋል።

ጉባኤው በፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ ሊካሄድ የተወሰነበት መሠረታዊው ምክንያት፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ የዛሬ 70 ዓመት በፊት በተጀመረበት እና እንዲሁም የበርሊን ግንብ የፈረሰበት 20ኛው ዓመት የሚዘከርበት ዓመት መሆኑ የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስረድተው፣ ይህ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ መልክ ያለው ታሪክ በሁሉም ሃይማኖቶች መካከል ውይይት ተደርጎበት ፖለቲካዊ ባህርይ ያለው የዓለማችን ታሪክ በሁሉም ሃይማኖትች መካከል በሚደረገው ውይይት የሚሰጠው የጋራው ምልሽ በጋራ ለማቅረብ ጥረት የሚያደርግ ጉባኤ ነው ካሉ በኋላ፣ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የአሲዚው መንፈስ በሁሉም ሃይማኖቶች መቀራረብ እንዲገለጥ ያነሳሱት የሁሉም ሃይማኖቶች ግኑንኝነት የሚያስታውስ ጉባኤ መሆኑም በማብራራት፣ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤው በክራኮቪያ እንዲካሄድ የወሰነበት ምክንያት የላቀ እና ፖላንድ ለምስራቁ ዓለም ቅርብ የሆነቸው የምዕራብ አገር በመሆኗ ጭምር እንደሆነም አብራርተዋል።

በመጨረሻም ቤተ ክርስትያን ይቅር በመባባል በእርቅ እና በሰላም ሂደት ያላት ተሳትፎ የላቀ መሆኑ የሚመሰክር እና ሁሉም አቢያተ ክርስትያናት በሁሉም አቢያተ ክርስትያናት አንድነት እንዲረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት የሚያነቃቃ ጉባኤ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስትያን ሕዝበ እግዚአብሔር የሚል ፍች ከሰጠበት ወዲህ ጀምሮ ቤተ ክርስትያን ማለት ሊቃነ ጳጳሳት ካህናት ደናግል ብቻ ማለት ሳይሆን ሁሉም በተለያየ ጥሪው የሚኖርባት የሕዝብ ጉባኤ ነች ስለዚህ የሁሉም ቤተ ክርስትያናዊ ኃላፊነት የሚጎላበት ጉባኤ ጭምር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.