2009-09-04 14:39:12

የአባ ኮሎምቦ የቀርብ ሥነ ሥርዓት


ጳጳሳዊ የግብረ ተልእኮ ማኅበር አባል አባ አውጉስቶ ኮሎምቦ በ 82 ዓመት እድሚያቸው እ.ኤ.አ. ባለፈው ነሓሰ 31 ቀን 2009 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ RealAudioMP3 ትላትና በተካሄደው የቀብር ሥነ ሥርዓት 40 ሺሕ ሕዝብ መሳተፉ ሲገለጥ። ኣባ ኮሎምቦ የጳጳሳዊ ግብረ ተልእኮ ማኅበር አባል በህንድ ለማገልገል ተልከው በአንድህራ ፕራደስ ክልል የተናቁት በጠና ስቃይ ላይ ወድቀው የሚገኙትን በጎሳ እና በሃይማኖት ሰበብ ተረግጠው እና ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ተብለው ለሚገለጡት ቅርብ በመሆን አለ አድልዎ እና ልዩነት የክርስቶስ ፍቅር በሕይወት የመሰከሩ ናቸው። ያገሪቱን ቋንቋ ጠንቅቀው የሚያውቁ በመንግሥት እና በክልሉ ህብዝ ዘንድ ተወዳጅነት የነበራቸው ካህን እንደነበሩም ኤሺያን ኔውስ ያሰራጨው ዜና ይጠቁማል።

የህይደራባድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማራምፑዲ ጆጂ በመሩት የፍትሓት ቅዳሴ 200 ካህናት መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ ሶስት የመንግሥት ልኡካን ሚኒስትሮች እና 40 ሺሕ ሕዝብ በቀብሩ ስነ ሥርዓት መገኘታቸውም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.