2009-09-04 14:37:02

የብፅዕት ማድረ ተሬዛ አመለካከት እና ትምህርት


የብፅዕት ማድረ ተረዛ ዘ ካልኵታ አመለካከት እና አስተምህሮ የሚገልጥ መጽሓፍ መታተሙ ሲገለጥ፣ መጽሓፉ በሲዲ መልክ ጭምር በድምጽ መቀረጹም ለማወቅ RealAudioMP3 ተችለዋል።

ይህ ስለ ብፁዕት ማድረ ተረዛ ዘ ካልኵታ ሕይወት አስተሳሰብ እና ትምህርት የሚገልጥ በሲዲ ተቀርጾ እና በመጽሓፍ ታትሞ እንዲቀርብ ካሪታስ በመባል የሚጠራው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር እና የኤውሮጳ የሰብአዊ ሃብት ጉዳይ የሚከታተለው ማእከል በጋራ በወጠኑት የባህል እና የህንጸት መርሃ ግብር መሠረት ያነቃቁት እቅድ መሆኑም ተገልጠዋል።

ሲዲው እና መጽሓፉ ለማስተዋወቅ በተካሄደው ግኑኝነት እንድ ጧት በእግዚአብሔር እጅ በሚል ርእስ ሥር ተወጥኖ ለፍጻሜ የበቃ ለአድማጭ እና ለአንባቢ መቅረቡ ሲገለጥ፣ ለተለያዩ ሃይማኖት ምእመናን እጅግ ደስ ማሰኘቱም ተመስክረዋል። በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር በተራመደበት ዓለም መደጋገፍ ስደት እና ድኽነት በሚታይበት ዓለም የሰአዊ መብት እና ፈቃድ አክብሮት እንዲነቃቃ የሚያግዝ የብፅዕት ማድረ ተረዛ ዘ ካልኩታ ትምህርት ያዘለ መፅሓፍ እና ሲዲ መሆኑ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.