2009-09-04 14:35:18

በኤወሮጳ ጥገኝነት ለሚጠይቁ ስደተኞች የመተዳደሪያ ደንብ


በኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ጥገኝነት ለሚጠይቁት ስደተኞች መብት እና ፈቃድ በሚመለከት አንድያዊ የጋራ ደንብ መሠረት ተገቢ መልስ ለመስጠት ይኸንን ለማስተዳድር የሚያግዝ የህብረቱ RealAudioMP3 የስደተኛ እና የተፈናቃይ ደንብ ከትላትና በስትያን የኤውሮጳ ኅብረት ምክትል ሊቀ መንበር ዣክ ባሮት በይፋ እንዳቀረቡ ተገለጠ። የዚህ ደንብ ዓላማም ወደ አባል አገሮች ለሚገቡት ጥገኝነት የሚጠይቁት ስደተኞችን በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እንዲሁም በኤሮጳው ህብረት የሰብአዊ መብት መሠረት የጥገኝነት ዋስትና ለመጠበቅ መሆኑ ተገልጠዋል።

የፒያቸንሳ ሊቀ ጳጳስ እና የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በኤውሮጳ ህብረት ልኡክ ብፁዕ አቡነ ጃኒ ኣምብሮሲዮ ይህ የኅብረቱ የጥገኝነት ጠያቂ ስደተኛ መተዳደሪያ ደንብ በማስመልከት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ ጥገኝነት የሚጠይቁት ስደተኞች ጉዳይ የሚያስተዳድር የኅብረቱ አንድ ወጥ ደንብ እንዲኖር መደረጉ አወንታዊ መሆኑ አብራርተው ሲጠበቅ የነበረ ውሳኔም ነው ብለዋል።

በዓለማችን ከድሆች አገሮች በማደግ ላይ ከሚገኙት ግጭት እና ጦርነት ፖሊቲካዊ፣ ማኅበራዊ ሰብአዊ ችግሮች ከሚፈራረቁባቸው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ከማይከበርባቸው አገሮች የተሰደደ ሕዝብ 10 ሚሊዮን እንደሚደርስ እና ከነዚህም ውስጥ 200 ሺሕ በኤውሮጳ ጥገኝነት አግኝቶ የሚኖር መሆኑ ተገልጠዋል። ይኸንን የህብረቱ የስደተኛው የመተዳደሪያ ደንብ ገቢራዊ የሚያደርግ እና የፖሊቲካ ጥገኞች ጉዳይ የሚመለከት አንድ የህብረቱ የጋራ ጽ/ቤት በ 2010 ዓ.ም. ተቋቁሞ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.