2009-09-02 13:59:43

ፓኪስታን


የፓኪስታን ክርስትያን ማኅበርሰብ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ዘንድ ባለው የወንጀል መቅጫ ሕግ ሥር ሃይማኖት እና ያምልኮ ሥፍራ ማርከስ ወንጀል መሆኑ በማብራራት ይኸንን ወንጀል የሚፈጽም የሚደርስበት ቅጣት RealAudioMP3 የሚያመለክተውን ሕግ በመቃወም የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ድረገት አነሳሽነት ፊርማ የመሰብሰብ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑ ተገልጠዋል።

ይህ በፓኪስታን ሕግ በወንጀለኛ መቅጫ ዘንድ ሰፍሮ ያለው ሃይማኖት እና የአምልኮ ሥፍራ ማርከስ ወንጀል ነው የሚለው እና የሚያስከትለው ቅጣት ሆን ተብሎ ባገሪቱ የሚገኙትን አናሳ ሃይማኖትች እና የነዚህ ሃይማኖት ምእመናንን ዒላማ በማድረግ የተወጠነ መሆኑ የገለጠው የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትሕ እና የሰላም ድርገት፣ አንቀጹ ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እንዲዘረዝ ጥሪ ማቅረቡ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። ይህ ድርገት ያቀረበው ጥሪ በሌሎች አናሳ ሃይማኖትች እና ምእመናን ድጋፍ ያገኘ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ አንቀጽ ይታደስ ዘንድ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. አገሪቱን ይመሩ በነበሩት በርእሰ ብሔር ሙሻራፍ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ እንደቀረም ፊደስ የዜና አገልግሎት በማስታወስ ቤተ ክርስትያን ሕጉ ገና አንድ ብሎ ቅድመ ንድፍ ሆኖ በኋላም ጸድቆ ላገልግሎት ከዋለበት እለት ጀምሮ ዘወትር ጸረ አናሳ ሃይማኖቶች ምእመናን መሆኑ በማብራራት ተቃውሞዋን ከማሰማት ወደ ኋላ እንዳላለችም የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.