2009-09-02 13:55:52

ጳጳሳዊ የጤና ጥበቃ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት


ጳጳሳዊ የጤና ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት እ.ኤ.አ. እፊታችን ህዳር ወር ለማካሄድ ወስኖት ስላለው የዓለም ዓቀፍ ጉባኤ መርሃ ግብር ለቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማቅረቡ ተገለጠ። RealAudioMP3 በተለያዩ የካቶሊክ ቤት ክርስትያን የጀሮ የመስማት ስሜት ለተነፈጋቸው ዜጎች ሓዋርያዊ አገልግሎት ለማቅረብ የሚል ሲሆን፣ ይህ ርእስ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍል በአቢያተ ክርስትያን ተገቢ ክብራቸው እንዲጠበቅና ከኖልዎ እቅድ ውጭ እንዳይሆኑ የሚያነቃቃ መሆኑ ተገልጠዋል።

የዚህ ጳጳሳዊ የጤና ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዞሞውስክ ባለፉት ቀናት የስብሰባው መርሃ ግብር ለቅዱስ አብታችን ባቀረቡበት ዕለት ይህ 24ኛው ዓለም አቀፍ ጠቅላይ ጉባኤ በቫቲካን ከህዳር 19 ቀን እስከ ህዳር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ይህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በቀጥታት የጀሮ የመስማት ስሜት የተነፈጋቸው የሚመለከት በመሆኑም የስብሰባው መርሃ ግብር በማዘጋጀት ሂደት የጀሮ የመስማት ስሜት የተነፈጋቸውን የሚደገፍ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ማኅበር መሳተፉም ብፁዕ አቡነ ዞሞውስኪ ገልጠው፣ ይህ ርእስ በስነ ማህበረሰብ፣ በስነ ሰብእ በስነ አእምሮ በስነ ሕክምናው ረገድ የሚደረገው ክትትል በመዳሰስ የጀሮ መስማት ስሜት የተፈጋቸው ቤተ ክርስያን የምታካሂደው ግብረ ኖልዎ በመዳሰስ አቢያተ ክርስትያን በዚህ ረገድ የሚሰጡት አገልግሎት ፈር ለማስያዝ መሆኑም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.