2009-09-02 16:37:44

የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ በትሪፖሊ፡


በሊብያ ትሪፖሊ ላይ የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ፡ በምዕራባዊ ሱዳን ዳርፉር ላይ እና የሱማሌ ግጭቶች ጨምሮ የክፍለ ዓለሚቱ ግጭቶች መሠረታዊ መፍትሔ እያፈላለገ መሆኑ ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

በዚሁ በየሕብረቱ ሊቀመንበር በሊብያው መሪ ሙዓመር ቃዛፊ የተጠራው ጉባኤ የሕብረቱ አባላት ሀገራት የመንግስታት መሪዎች እና ወኪሎች ተሳታፊ መሆናቸው ይህ ከትሪፖሊ የደረሰ ዜና ያመለክታል።

በዚሁ የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተገኝተው ክፍለ ዓለሚቱ ትኩረት የሰጠ ንግግር ካደረጉ የሀገራት መሪዎች የሊብያው መሪ ሙዓመር ቃዛፊ የሱዳን ፕረሲዳንት ዑመር ሐሰን አል በሺር የአልጀርያ መሪ ፕረሲዳንት ዓብደል ዓዚዝ ቡታፍሊቃ የዚምባብወ መሪ ፕረሲዳንት ሮበርት ሙጋበን እና የታንዛንያው ያካታ ኪክወተ እንደሚገኙባቸው ተነግረዋል።

የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በአህጉሪቱ የሚካሄዱ የውስጥ ግጭቶች ለእድገት እንቅፋት መሆናቸው በመገንዘብ ግጭቶቹ እንዲገቱ ጥረቱ ለማጠናከር መስማማታቸው ከቦታው የደረሰ ዜና ገልጸዋል።

በዚሁ ዜና መሠረት የአፍሪቃ ሕብረት መሪዎች ለሱማሌ የሽግግር መንግስት ሁለንትናው ድጋፍ ለመስጠት እና ሀገሪቱ ውስጥ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለመጨመር በሚቻልበት ጉዳይ በሰፊው ተወያይተዋል።

ሶስት ሺ የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ሱማሌ ውስጥ እንደሚገኙ የሚትወቅ ሲሆን፡ መሪዎቹ የሰላም አስከባሪ ኀይሉ ወደ ስምንት ሺ ከፍ ለማድረግ እቅዱ እንዳላቸው አብሮ የደረሰ ዜና ያመለክታል።

በፕረሲዳንት ሸሪፍ አህመድ የሚመራው የሱማሌ የሽግግር መንግስት አልሻባብ ከተባለ አክራሪ ድርጅት ጋር እየተዋጋ መሆኑ ዜናው አስታውሰዋል።

የአፍሪቃ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምዕራባዊ ሱዳን ዳርፉር ላይ በጋራ ሰላም አስከባሪ ኀይሎች ማስፈራቸው እና የክፍለ አለሚቱ መሪዎች በዚሁ ክልል ሰላም ለማስፈን በሚቻልበት ጉዳይም ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው ተነግረዋል።

የአፍሪቃሕብረትመሪዎች ጉባኤ ከሚካሄድበት ቦታ የደረሰ ዜና እንደሚያመለክተው፡ መሪዎቹ በማዳካስካር እና ጒነአ ላይ የተካሄዱ መፈንቅለ መንግስታት አውግዘው ሕጋዊ መንግስታት የሚተከሉበት ሁኔታ በተመለከተም ተነጋግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.