2009-09-02 13:57:26

የቅስት መንበር የዜና እና የማህተም ክፍል ዋና ኃላፊ ማረጋገጫ


በቅርቡ በኢጣሊያ አቨኒረ ለተሰየመው የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አስተዳዳር ዲኖ ቦፎ በተመለከተ ባንድ የኢጣሊያ ዕለታዊ ጋዜጣ ታትሞ የቀረበው ትችት ከእውነት የራቀ መሆኑ RealAudioMP3 ከተለያዩ አካላት ምላሽ እየተሰጠበት ሲሆን፣ የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ እንዲሁም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በዲኖ ቦፎ ላይ የተሰነዘረው የወቀሳ ሐተታ አሉ ባልታ ነው ሲሉ ምላሽ በመስጠት፣ የቤተ ክርስትያን ለቦፎ ያላት አክብሮት እና ቅርበት ጽኑ መሆኑ የሰጡት መገልጫ፣ የቅድስት መንበር የዜና እና የማህተም ክፍል ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አረጋገጠውታል።

የቤተ ክርስያን የመገናኛ ብዙኃን ዓላማ ከሌሎች የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ለየት ያለ መሆኑ ለማንም የተሰወረ እንዳልሆነም ኣባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን በማንም የአሉ ባልታ ወሬ እትደናገጥም የሚዘነዘርባት የሐሰት ወሬ እውነትን በመመስከር እንደምትወጣውም በመግለጥ ለቦፎ ትብብራቸውን እና አድናቆታቸው አረጋገጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.