2009-09-02 13:58:43

ቅዱስ አባታችን የቅዱስ ኤጂዲዮ ማህበር አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ


ቅድስቱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላትና በስትያ የኢጣልያ የካቶሊክ የቅድስቲ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ መሥራች አንድረያ ሪካርዲ እንዲሁ የማህበረሰቡ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ RealAudioMP3 እና የማኅበርሰብ መንፈሳዊ መሪ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጠ።

በዚህ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ኤጂዲዮ ባከበረች አጋጣሚ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዚህ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ የበላይ ተጠሪዎችን ተቀብለው ባነጋገሩበት ዕለት፣ ይህ ማኅበር እ.ኤ.አ. ከመስከረም 6 ቀን እስከ መሰከረም 8 ቀን 2009 ዓ.ም. “ሰዎች እና ሃይማኖቶ’ በሚል ርእስ ሥር በክራኮቪያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ለቅዱስነታቸው በይፋ አስታውቀዋል።

የዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የ 2009 ዓ.ም. ጉባኤ በማስመልከት የማኅበርሰብ ሊቀ መንበር ቪቸንዞ ፓሊያ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ጉባኤው በፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ ሊካሄድ የተወሰነበት መሠረታዊው ምክንያት፣ ሁለተኛው የዓለም አቀፍ ጦርነት፣ የዛሬ 70 ዓመት በፊት በተጀመረበት እና እንዲሁም የበርሊን ግንብ የፈረሰበተ 20ኛው ዓመት የሚዘከርበት ዓመት መሆኑ ገልጠው፣ እነዚህ ሁለት የታሪክ ገጠመኞች የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ጉባኤውን በፖላንድ እንዲያካሂድ እንደገፋፋው አብራርተው፣ ከዚህች የጦርነት እውድማ ሆና ከነበረቸው ከተማ እና ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ከተወለዱባት አገር የጦርነት እና የግጭቶች መነሻ የሆኑትን ምክንያቶች ወደ ጎን በማድረግ አለማችን ለሰላም እንዲታጠቅ ለማነቃቃት በማቀድ ነው ብለዋል።

በሰላም ግንባታ የቤተ ክርስትያን የሰላም ጥሪ በሁሉም ክፍለ ዓለም ተሰሚነት ያገኝ ዘንድ የሰላም ጥሪ የሚቀርብበት መድረክ እንደሚሆን ገልጠዋል።

ለጦርነት እና ለሰው ልጅ እልቂት የቀረቡት ምክንያቶች በሰላም እና በመቀራረብ ምክንያት እንዲወገድ የጦርነት እና የእልቂት ሥፍራ ከሆኑት በመነሳታ የታሪክ ስሕተቶች ዳግም እንዳይከሰቱ መሠረታዊን ምክንያት ለማጉላት የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር የዘንድሮው ጉባኤ በክራኮቪያ ለማካሄድ መወሰኑ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.