2009-09-02 14:00:54

ሕንድ


ዘንድሮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ባለው የካህናት ዓመት ምክንያት በሕንድ የጉጃራት ግዛት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለመላ ዓለም የክርስትና መለያ ማብሰር RealAudioMP3 እና ክርስትናን መመስከር በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ እንደሚከበር ተገልጠዋል።

የጉጃራት ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ማክዋን ባቀረቡት ጥሪ መሠረት የሰበካው ውሉደ ክህነት፣ ገዳማውያን በጠቅላላ የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት በሰበካው በሚገኘው የናዲያድ የኖልዎ ማእከል የካህናት ጠባቂ ቅዱስ ጆቫኒ ማሪያ ቪያነይ በተመለከተ ሰፊ ዓውደ ጥናት ማካሄዱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል። በተካሄደውው ዓውደ ጥናት ብፁዕ አቡነ ማክዋን ባሰሙት ንግግር በአገሪቱ የውሉደ ክህነት ሁኔታ እና የክልሉ ክርስትያን ማኅበርሰብ የሚፈታተኑት በተለይ ደግሞ አክራሪያን የሂዱ ምእመናን በሚፈጥሩት ውጥረት እና ጥቃት ሳቢያ የሚጋፈጠውን ማህበራዊ ሰብአዊ ችግሮች በመዳሰስ እምነቱን በመመስከር ላይ እንደሚገኝ ማብራራታቸው የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.