2009-09-02 16:19:44

ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ከተጫረ ሰባ ዓመታት አሰቆጥረዋል ፣


በጀርመን ርእሰ ከተማ በርሊን ላይ የጀርመን ናዚዎች በፖላንድ ላይ ዓመጽ የፈጸሙበት ሰባኛ ዓመት ተዘክሮ መዋሉ ከዚሁ ቦታ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል ።

የጀርመን እና የፖላንድ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በበርሊን ዳንዚግ ከተማ አቅራብያ ቨስተር ፕላተ በተባለ ቦታ በሚገኘው ቤተክርስትያን ተገኝተው በጋራ ከሰባ ዓመታት በፊት ናዚዎች ፖላንድን ባጠቁበት ግዜ የዚሁ ጥቃት ሰለባ ስለሆኑ ሰዎች መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው እና መጠለያቸው ይህ ከበርሊን ከተማ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።

የሁለቱ ሀገራት ካቶሊካውያን ጳጳሳት የሁለቱ ሀገራት አብያተ ቤተክርስትያናት እግዚአብሔር ለሁለቱ ሀገራት እና ለመላ ዓለም ሰላሙ ይሰጥ ዘንዳ መጠለያቸው ዜናው በተጨማሪ አብራርተዋል።

በዚሁ በበርሊን በዳንጺግ አቅራብያ የተካሄደው ሥርዓተ ቅዳሴ እና ጸሎት የሀገሪቱ መራሂተ መንግስት ቻንስለር ኤንገላ መርክል የሩስያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላዲሚር ፑቲን የጣልያኑ አቻቸው ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ተሳታፊ መሆናቸው የበርሊኑ ዜና አስገንዝበዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት የዓለም ህዝቦችን ለዓቢይ ስቃይ ያዳረገ አስከፊ ድርጊት መሆኑ ቀደም ሲሉ መግለጣቸው የሚታወስ ነው።

ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ያደረሰው ውድመት አስታውሰው የሰው ልጅ ራሱ በራሱ ያዳረሰው አስከፊ እልቂት መሆኑ የትውልድ ሀገራቸው ፖላንድ እና ጀርመን በጐበኙበት ግዜ መግለጣቸው ያማይዘነጋ ነው ።

በሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ፍጻሜ የፖላንድ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ለጀርመናውያን ጳጳሳት ምሕረት ሰጥተን ምሕረት እንጠይቃለን በማለት የዕርቅ መልእክት ማስረከባቸው የማይዘነጋ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጠባሳ እና አስከፊነት ምሕረት ሰጦ ምሕረት በመቀበል ብቻ ሊድን እንደሚችል ይገልጣሉ ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እኤአ ግንቦት አስራ ዘጠኝ ቀን 2005 ፖላንድ እና ጀርመን በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ያሳለፉት ግዜ አስታውሰው የፖላንድ ዜጋ የሆኑት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በጀርመን ዜጋ በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ መተካት የመንፈስ ቅዱስ ድርጊት ብቻ መሆኑ ገልጠው ነበር ።

ሁለቱ አርእሰ ሊቃን ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በለተኛ የዓለም ጦርነት የስቃይ እና የጥፋት ማእከል የነበረውን አውስ/ሽቪትጽ በመጐብኘት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን መግለጣቸው የማይዘነጋ ነው ።

ግንቦት ሀያ ስምንት ቀን 2006 እንደ ኤውሮጳ አቈጣጠር ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አውስሽቪትጽ በጐበኙበት ግዜ ርእሰ ሊቃነ ከኔ በፊት የነበሩ ውድ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዳደረጉት ሁሉ እነሆ እኔም እዚህ አውስሽዊትቭ ላይ በመገኘት የሚሰማኝ ሐዘን በመግለጥ የእኩይ ተግባሩ ሰለባ ለሆኑት ሁሉ ጸሎቴ አሳርጋለሁኝ በማለት የናዚ ተግባር ማውገዛቸው ይታወሳል።

የጀርመን ናዚ ወንጀለኞች በእብሪት ተወጥረው በሰዎች ሕይወት ላይ የፈጸሙት ተግባር ተወዳዳሪ የሌለው እኩይ ተግባር መሆኑም በመሬት እና ሐዘን ገልጠው እንዲህ ዓይነቱ ተግባር እንዳይፈጸም የዓለም ህዝቦች በንቃት ሰላም እንዲጠብቁ መማጸናቸውም የትናትና ትዝታ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.