2009-08-31 13:56:40

ዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ


በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክልል የጎበኙት የዩኒሰፍ የሕጻናት ጉዳይ የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ አስተዳዳሪ ኤን ቨነማን በዚህች አገር ገና ያልተወገደው የአመጽ RealAudioMP3 እና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የወሲብ በደል በመቃወም ይህ ጸረ ሰብአዊ ድርጊት እንዲወገድ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ጦርነት በይፋ እ.ኤ.አ. 2003 ዓ.ም. ያበቃለት ቢሆንም ቅሉ የጦር ኃይል አባላት በተለያዩ መንደሮች ዘልቀው በመግባት በሴቶች ላይ የወሲብ አመጽ ከመፈጸም ኢሰብአዊው ተግባራቸው እንዳልተላቀቁ ቨነማን ገልጠው፣ የዚህ አመጽ ሰለባ የሆኑት ሴቶች ከሚደርስባቸው ሰብአዊ ስነ አእምሮአዊ ችግር ባሻገርም ከማኅበርሰብ እና ከቤተሰቦቻቸውም ተነጥለው ለመኖር በሚያስገድድ ኋላ ቀር ባህል የሚደርስባቸው ተጨማሪው ችግር ጠቅሰው፣ ለርሃብ እና ለመፈናቀል አደጋም ብሎም ለሞት አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ በማሳሰብ ከዚህ ዓይነት አስነዋሪ እና አስከፊው ጸረ ሰብአዊ ግፍ እንዲላቀቁ የዓለም ማኅበርሰብ እና መንግሥታት የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ያደራ ጥሪ አስተላልፈዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.