2009-08-31 13:59:15

የደቡብ አፍሪካ ክልል አገሮች ካህናት ምክር ቤት


የአፍሪካ ደቡባዊ ክልል አገሮች ካህናት በደቡብ አፍሪካ በምትገኘው በማሪያንሂል በሚገኘው ገዳም ስለ የካህናት ወቅታዊው ሁኔታ ርእስ ለመወያየት መሰብሰባቸው ሲገለጥ። ይህ በያመቱ የደቡብ አፍሪካ አገሮች RealAudioMP3 እነርሱም የቦትስዋና ደቡብ አፍሪካ እና ስዋዚላንድ አገሮችን ያጠቃለለው የካህናት ምክር ቤት የሚያካሄደው ስብሰባ ሲሆን፣ ዘንድሮ እየታሰበ ያለው የካህነት ዓመት በነዚህ ክልል አገሮች በካህናት ላይ የሚፈጸመው አመጽ እና እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ያፍሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊው ማህበራዊው እና ሰብአዊው አገልግሎት ለማስተዋወቅ አጋጣሚ እንዲሆን በተሰኙት ርእሶች እንደሚወያዩ ተገልጠዋል።

የዚህ የደቡብ አፍሪካ አገሮች የካህናት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጆሃንስበርግ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቡቲ ጆሴፍ ቲጋለ ካህናት ጥሪያቸው በየቀኑ እያደሱ እንዲኖሩ እና የሚሰጡት መንፈሳዊ ማህበራዊ እና ሰብአዊ አገልግሎት የልማድ ተግባር ሳይሆን የጸሎት ውጤት በየቀኑ የሚታደስ እንዲሆን በተካሄደው ስብሰባ አደራ ማለታቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ሕትመቱ አመልክቶታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.