2009-08-31 13:57:57

የተፈጥሮ አካባቢ አየር ጤና ተንታኝ ዓለም አቀፍ ማኅበር


የተፈጥሮ እና የአካባቢ አየር ጤና የሚወያይ ሶስተኛው የዓለም አቀፍ የስነ ተፈጥሮ አየር ንብረት ሊቃውንት ዛሬ በጀነቭ መከፈቱ ተገለጠዋል። ይህ የሚካሄደው ጉባኤ የተፈጥሮ የአየር ንብረት RealAudioMP3 ትንተና፣ ስለ ትንተናው በመገናኛ ብዙሃን በየዕለቱ ማሳወቁ በተፈጥሮ የአየር ንብረት ለወጥ የሚከሰቱትን ችግሮች ለመቆጣጠር የተለያዩ ውሳኔዎችን እውን ለማድረግ የሚያግዝ ነው በሚል ርእስ ሥር የሚሄድ ሲሆን፣ የሚኖረው የአየር ጸባይ ቀድሞ ማሳወቁ የአየሩ ጸባይ ሊያከትለው የሚችለውን ችግር ጭምር ከወዲሁ ለመቋቋም የሚያግዝ ስልት ለመወጠን የሚያነቃቃ መሆኑ በሰፊ ስነ ጥንትዊ ማብራሪያ የሚሰጥበት መድረክ እንደሆነ እና በተለይ ደግሞ የሚሰጠው የአየር ንብረት ቅድመ ትንተና በተመለከተ የሚሰጠው መገልጫ እና የአየር ንብረት ለውጡ የሚያስከትለው ችግር ለመጋፈጥ የሚደረገውም ጥረት አለም አቀፋዊ ቅርጽ ለማስያዝ የሚቻልበትን መንገድ ለመቀየስ ብሎም አንድ የዓለም አቀፍ ማኅበር እንዲቋቋም ጥሪ እና ሓሳብ የሚቀርበት መድረክ መሆኑም ከወዲሁ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.