2009-08-31 13:55:45

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት


የዛሬ 70 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. መስከረም 1939 ዓ.ም. የተቀጣጠለው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በማስመልከት የጀርመን እና የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት በጋር ለሰላም እና ለሰው ልጅ RealAudioMP3 ከጥላቻ ነጻ የሚያደርግ ህያው እና ትጋት የተሞላው ሕንጸት ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ያሰመሩበት መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ። ለሁሉም ሕዝቦች ጥቅም የሚበጅ እና ዘላቂው ሰላም ይቅር በመባባል እና በእርቅ መንፈስ ብቻ የሚጨበጥ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ማብራራታቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ በርሊን በሚገኘው በቅዱስ ኤድቪገ የሁለቱ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ትላትና በጋራ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ተገልጠዋል። በፖላንድ በዳዚቻ ከተማ ነገ እ.ኤ.አ. መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ሁለተኛው የአለም ጦርነት ያስጀመረው የመጀመሪያ የፍንዳታ ጥቃት በተጣለባት ከተማ ዌስተርፕላተ መሥዋዕተ ቀዳሴ እንደሚቀርብ ሲነገር፣ በሚካሄደው የተዘክሮ በዓል የሩሲያ መራሔ መንግሥት ቭላድሚር ፑቲን የሚገኙባቸው የተለያዩ አገሮች መሪዎች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችለዋል።

ሮማ በሚገኘው በሉምሳ መንበረ ጥበብ መምህር የታሪክ ሊቅ ፕሮፈሶር ቪክቶር ዛልስላቭስክይ ስለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተመለከተ ከቫቲካን ረድዮ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፣ ዓለማችን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ይረሳዋል ማለት ዘበት ነው፣ የቡዙ አገሮች በተለይ ደግሞ የሩሲያ ማኅበራዊው መለያ እንዲረጋገጥ ያደረገ መሆኑም ገልጠው፣ በጦርነቱ ዘመን ተቀናቃኝ በነበሩት አገሮች መካከል የነበረው መቃቃር እንዲወገድም የተደረገው ጥረት በማስመከት እንደ አብነትም በጀርመን እና በፖላንድ፣ በፖላንድ እና በኡክራይን መካከል የተረጋገጠው ህዝባዊ እርቅ ጠቅሰው፣ ይህ ሂደት የምስራቅ ኤውሮጳ አገሮች የኤውሮጳ ኅብረት አባል አገሮች መሆን በጀመሩበት ማግሥት በአህጉራቱ እና በሕዝቦች መካከል የታየው መቀራረብ እና ትብብር እንዲከሰት ማድረጉም በማስታወስ፣ በጦርነቱ ተቀናቃኝ አገሮች መካከል የነብረው ፖሊቲካዊ ማህበራዊ ቅሬታ እና ቂም በቀል ሥፋራ እንዳያገኝ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተክርስትያን የተጫወተቸው ሚና የሚደነቅ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.