2009-08-28 13:56:04

ዳርፉር


በዳርፉር የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍርካ ህብረት ጣምራው የሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ማርቲን ሉተር አግዋይ ዳርፉር የጦርነት አውድማ ኣይደለችም እንዳሉ RealAudioMP3 ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በክልሉ የነበረው ጦርነት ረግቦ አልፎ አልፎ ይታይ የነበረው የቶክስ ግጭት እና የወንበዴነት ሴራ እጅግ እየቀነሰ መሆኑ አግዋይ ገልጠው፣ ስለዚህ በክልል የነበረው ጦርነት እየተወገደ ነው እንዳሉም የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል። ይህ እ.ኤ.አ. ከ 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የደም መፈሳሳ ክልል ሆኖ መቆየቱ እና የካርቱም መንግሥት መሠረት 10 ሕዝብ እንደ የተባበሩት መግሥታት መግለጫ መሠረት 300 ሺሕ ሕዝብ ለሞት አደጋ ያጋለጠው ጦርነት ሲካሂድበት መቆየቱ የሚዘከር ሲሆን በክልሉ ሰላም ለማስፈን የተደረገው ጥረት አቢይ ውጤት እያስገኘ ነው እንዳሉም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.