2009-08-28 13:52:28

የመቃብር ሥፍራ የማርከስ ተግባር በግሪክ


በግሪክ ካናይ በሚገኘው የካቶሊክ የመቃብር ሥፍራ የጥፋት አደጋ መጣሉ ሲገለጥ፣ የክልሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተፈጸመው የሙታን መቃብር ሥፍራ የማርከስ ተግባር አሳሳቢ መሆኑ RealAudioMP3 በመጥቀስ የአገሪቱ የፍትሕና የማኅበራዊ ሥርዓት አስከባሪ ጉዳይ ሚኒስትር የተፈጸመው ድርጊት እንዲከታተለው እና ተመሳሳይ አደጋ እንዳይጣል የጥበቃ ውሳኔ ያስተላልፍ ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።

ስለ ጉዳይ በተመለከተ በግሪክ የስይሮስ ሚሎስ እና ሳንቶሪኒ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት የክሬታ ሰበካ ሓዋርያዊ አስተዳዳሪ እና የግሪክ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፍራግኪስኪስ ፓፓማኖሊስ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ መጀመሪያ የደረሰው የጥፋት አደጋ በመቃብር ሥፍራው የሚዘዋወሩት የያደንዛዥ እጸዋት ሱሰኞች ወይንም የመቃብሩ ሥፍራ እመሀል ከተማ የሚገኝ በመሆኑ ብዙዎች ከሞት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ስነ አእምሮአዊ ችግር ያለባቸው ግለ ሰቦች የፈጸሙት ይሆናል የሚል ግምት ነበር፣ ሆኖም ግን አደጋው በተደጋጋሚ የሚፈጸም በመሆኑም ጉዳዩ በይሆናሉ የሚታለፍ ሳይሆን ክትትል ተደርጎ ተጠያቂው መለየቱ እንደሚበጅ ቤተ ክርስትያን ለሚመለከተወ አካል አቤት እንዳለች ገልጠዋል።

ስለ ተፈጸመው አደጋ በተመለከተ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን እምብዛም እንደማይናገሩ ገልጠው፣ የክሬታ ቤተ ክርስትያን የአድልዎ እና የኢፍትኅዊነት ድርጊት ሰለባ ሆና እንደነበርም አስታውሰው፣ ብዙ ኢፍትኃዊ ተግባሮች ለሕግ ለማቅረብ ተገቢ ሆኖ እያለ ነገር ግን የካቶሊክ ቤተክርስትያን የደረሰባት በደል ወንጀል ነው ብሎ ለሕግ ለማቅረብ የሚያግዱዋት ብዙ ምክንያቶች እንዳሉም ገልጠዋል። የግሪክ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በአገሪቱ መንግሥት ምንም ዓይነት እውቅና የሌለው የአተኔ ርእሰ ሰባካ እውቅና አላገኘም፣ ቤተ ክርስትያን ይፋዊ እውቅና ያላገኘች በመሆኗም ጉዳት ቢደርስባትም እንደ ቤተ ክርስትያናዊ መዋቅር ክስ ለማቅረብ መብት የላትም ካሉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. በክልሉ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሳቢያ የተጎዱት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን፣ ቤተክርስትያንዋ በአገሪቱ መንግሥት እውቅና የሌላት በመሆኗም መንግሥት ከወጠነው የመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሳትሆን መቅረቷንም አስታውሰዋል። በካቶሊክ እና በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታን በካከል ጥሩ ግኑኝነት አለ ቢባልም ግኑኝነት ይፋዊ እንዳለሆነ ገልጠው የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.