2009-08-28 13:57:23

ኬኒያ


የኬኒያ መንግሥት በቅርቡ በአገሪቱ ሰሜናዊ እና መካከለኛው ክልል ባንዳንድ ሕጽናት ላይ የታየው የሳንባ በሽታ እግምት ውስጥ በማስገባት ካምስት ዓመት እድሜ በታች ለሆኑት ሕጻናት RealAudioMP3 የጸረ ሳንባ በሽታ ክትባት እንዲሰጥ ባነቃቃው የጸረ ሳንባ መሽታ የክትባት ዘመቻ ምክንያት ለ 350 ሺሕ ሕጻናት ክትባት እንደሚሰጥ የኬኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒ. ቤትት ሙጎ አስታውቀዋል።

መንግሥት ያስተላለፈው ውሳኔ እግብር ላይ ለማዋል ግማሽ ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈግል ሲገለጥ፣ የክትባት እቅድ በሽታው በታየበት ወቅት የሚነቃቃ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው የጤና ጥበቃ ስልት መሸኘት እንዳለበት እና እንዲሁም ባንዳንድ ክልሎች የክትባት መድኃኒት ተገቢ እና አስፈላጊ ሆኖ እያለ የወሊድ መጠን ለመቆጣጠር የሚያገለግል ነው እየተባለ የሚነዛው ከእውነት የራቀ የሐሰት ዘመቻ መጠንቀቅ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሕጻናት ሕይወት ከሞት አደጋ ማዳን የሁሉም ኃላፊነት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.