2009-08-28 13:54:24

ስደተኛ ማስተናገድ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ሓላፊነት ነው

 


በኢጣሊያ የቪቸንዛ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ ቸዛረ ኖሲሊያ በቅርቡ ወደ ኢጣሊያ ለመግባት ከሊቢያ የተነሱት የሕገ ወጥ ስደተኞች ያጋጠማቸው ዘግናኝ የሞት አደጋ ምክንያት በኢጣሊያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል በኢጣሊያ RealAudioMP3 ዜጎች እና በስደተኞች መካከል ስላለው ግኑኝነት እና በዚሁ የኢጣሊያ ክልል የሚኖሩት ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሰው ልጅ ሕይወት በባህር ጉዞ ሲቀጭ ዝም ብሎ ማየቱ ወንጀል እና ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው ካሉ በኋላ፣ ስደተኛው እና የሕገ ወጥ ስደተኛ በማስተናገድ ሰብአዊነት እና የማህበራዊ ግዴታ መመስከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ብዙዉን ጊዜ የመገናኛ ብዙኃን በሰሜናዊ ምስራቅ የኢጣሊያ ክልል ስለ ሚኖሩት ስደተኞች እና በክልሉ ስለ ስደተኛ ያለው ግምት የሚሰጡት ዜና እና መግለጫ ከእውነት የራቀ ነው፣ ስደተኛው ከተስተናገደበት አገር ጋር ተዋህዶ እንዲኖር የሚደረገው ማህበራዊ ጥረት በአስተናጋጅ እና በተስተናጋጅ አገር ህዝብ መካከል የሚደረግ መሆን ይገባዋል። ስደተኛው ማኅበረሰብ ለመዋሃድ ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።

ህዝብ ደህንነትን እና ጸጥታን ይሻል፣ ሆኖም ግን የደህንነቱ እና የጸጥታው ጉዳይ ከስደተኛው ጉዳይ ጋር የተጣመረ መሆን የለበትም ብለዋል። ብዙዉን ጊዜ ሕዝቦች የስደተኛው ብዛት የጸጥታ እና የደህንነት መናጋት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ስጋት አለው፣ አንዳንድ የፖለቲካ አካላት እና ሰልፎች ጉዳዩ መፍትሔ እንዲያገኝ በሳል ጥረት ከማድረግ ይልቅ ይኽንን የዜጎች ሥጋት የራሳቸውን ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት እንደ መሳሪያ ሲጠቀሙበት ይታያል፣ ካሉ በኋላ፣ ስደተኛው ማኅበርሰብ በተስተናገደበት አገር ተዋህዶ እንዲኖር የሚያግዙ መርሃ ግብሮች እግብር ላይ እየዋሉ ናቸው አዝማሚያውም ፈር እየያዘ መምጣቱንም ገልጠው፣ በርግጥ መንግሥት እና የፖለቲካው ጉዳይ ይኸንን የስደተኛውን ጉዳይ ለማስተዳዳረ አቢይ ጥረት እና ፍላጎት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ ታውቆ መንግሥት የሚደነግገው የስደተኛው መተዳዳሪያ ሕግ የሰብአዊነት እና የተቀባይነት ያስተናጋጅነት ባህል የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምደመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.