2009-08-26 13:26:26

አፍጋኒስታን


በአፍጋኒስታን በተካሄደው ህዝባዊ ምርጫ ለምርጫው የቀረቡት እጮዎች ውስጥ ርእሰ ብሔር ሓሚድ ካርዛይ አሸናፊ ነኝ ሲሉ በምርጫው የወደሩት የሓሚድ ካርዛይ ዋነኛ ተፎካካሪ እብዱላህሕ አብዱላሕ RealAudioMP3 የተካሄደው ምርጫ የተጭበረበረ ነበር ብለዋል። በምርጫው የወደሩት እጩዎች ገና የምርጫው ውጤት በይፋ ከመገለጡ በፊት የሚሰነዘረው አስተያየት አላስፈላጊ ነው በማለት የምርጫው ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በመግለጥ፣ የተካሄደው ምርጫ ውጤት በተገለጠበት ማግሥት የርእሰ ብሔር ሓሚድ ካርዛይ እና የተፎካካሪያቸው አብዱላሕ አብዱላሕ አስተያየት ለግጭት እና ለአመጽ ጠንቅ እንዳይሆን አሳስበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለመ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ልዩ ወኪል ሆልብሩክ ከትላንትና በስትያ ካቡል መግባታቸው ሲገለጥ፣ ከሁለቱ እጩዎች ማለትም ከርእሰ ብሔር ሓሚድ ካርዛይ እና ከዋነኛው ተፎካካሪያቸው አብዱላሕ አብዱላሕ ጋር ተገናኝተዋል። አቀፍ ማኅበርሰብ መንግሥታት በምርጫው የወደሩት ዕጩዎች ሁሉ ምርጫው በተመለከተ ገና ውጤቱ በይፋ አለመገለጡ ተረድተው በትዕግሥት ውጤቱን መጠባበቅ እንዳለባቸውም አስተያየት ሲሰጡ፣ የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት መንግሥት የምርጫው ሂደት አስተማማኝ አልነበረም በማለት ግልጽነት የጎደለው ነው ሲል ትችት መሰንዘሩ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.