2009-08-26 13:22:13

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት


የዛሬ 70 ዓመት በፊት እ.ኤ.አ. መስከረም 1939 ዓ.ም. የተቀጣጠለው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በማስመልከት የጀርመን እና የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት በጋር ለሰላም እና ለሰው ልጅ ከጥላቻ ነጻ የሚያደርግ ህያው እና ትጋት የተሞላው RealAudioMP3 ሕንጸት ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ የሚያብራራ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ። ለሁሉም ሕዝቦች ጥቅም የሚበጅ እና ዘላቂው ሰላም ይቅር በመባባል እና በእርቅ መንፈስ ብቻ የሚጨበጥ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ማብራራታቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ሁለተኛው ያለም ጦርነት የዛሬ 70 ዓመት በፊት የጀርመን የንዚው የመከላከያ ኃይል ፖላንድን በመውረር ያስጀመረው ጦርነት ታሪክ ያስከተለው እልቂት እና አመጽ ባለፈው ታሪክ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን መጪው ሕይወት ነጻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያገፋፋ ጸረ ጦርነት ባህል የሚያነቃቃ መሆን እንደሚገባው የጀርመን እና የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት አብራርተዋል። የናዚ ፖለቲካዊ ጽንሰ ሐሳብ ማስተግባሪያው እልቂት እና አመጽ ሌላውን መጨቆን ማጥፋት በጠቅላላ ሌላውን ድምጥማጡን በማጥፋት ለመበዝበዝ ለባርነት አደጋ መዳረግ የሚለው የሚከተለው ጸረ የሰው ልጅ መንገድ ሲሆን በአይሁድ በዘላን የኤውሮጳ ህዝብ ጎሳ እና በአካሉ ስንኩላን በተቃዋሚ አካላት ላይ ያስከለው እልቂት የሚዘገንን ነው። ይኸንን አሰቃቂው የአለማችን የታሪክ ምዕራፍ መዘከር ተመሳሳይ አሰቃቂው አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ለመጸለይ እና የሰላምን ባህል ለማስፋፋት ቆርጦ መነሳት ማለት መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባስተላለፉት የጋራ መልእክት ያብራራሉ።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የኮሙኒዝም ሥርዓት ተቀባይነቱ ገኖ እያለም ፈላጭ ቆራጭ በመሆኑ ባንድ አገር በሕዝቦች መካከል ለመከፋፈል ያሳደረ እና ለጨቋኝ መንግሥት በር የከፈተ መሆኑም የገለጡት የሁለቱ አገሮች ብጹዓን ጳጳሳት በማከል የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የዓይን ምስክር በእድሜ መግፋት ምክንያት እየጎደለ በመሆኑም ስለ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና ያስከተለው እልቂት ለወጣቱ ትውልድ በማስተማር ተመሳሳይ ዛቻ እንዳይከሰት የሰላም ዋስትና እንዲጨበጥ የሰላም ህንጸት ማግኘት እንድሚኖርበትም አሳስበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.