2009-08-24 14:20:43

የፔክስ ሰበካ ሺህኛው የምስረታ ዓመት መጠናቀቅ


በሃንጋሪ የፔክስ ሰበካ ሺሕኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት ባገሪቱ ሲካሄድ የሰነበተው መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር መጠናቀቁት ተገለጠ። ለበዓሉ መዝጊያ ቅዱሱ አብታችንን ወክለው ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የቪየና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ክርሶትፈር ሹዩንበርን ባሰሙት ስብከት እምነትን እና ሃይማኖትን መንፈሳዊነት ችላ የሚለው ማመን እና አለ ማ RealAudioMP3 መን ያው ነው የሚለው የሰው ልጅ ለሞት ባህል የሚመራው የሚያስከትለው ችግር ለመጋፈጥ አትፍሩ፣ ክርስቶስን ፈልጎ አግኝቶ ለመከተል ወንጌሉን ላልደረሳቸው ለማድረስ እትፍሩ እንዳሉ ተገልጠዋል።

በበአሉ የተገኙት እና የመዝጊያውን የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የመሩት ብፁዕ ካርዲናል ሹዩበርን ያሰሙት ስብከት እና የፒክስ ሰበካ ምሥረታ በተምለከተ የቫቲካን ረድዮ የሃንጋሪ የራዲዮ ስርጭት ጋዜጠኛ ማርታ ቨርትሰ ባቀረቡት ዘገባ፣ ለሃንጋሪ እንዲሁም በኤውሮጳ እና በተለይ ደግሞ ለካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ታሪክ አቢይ ምዕራፍ መሆኑ ገልጠው፣ ሰበካው በቅዱስ ንጉሥ ስቴፋን መቋቋሙንም ዘክረው፣ ለኤውሮጳ ክርስትና አቢይ እና ልዩ ትርጉም ያለው የክርስትና የታርክ ምዕራፍ ነው ብለዋል። በሚስጢረ ጥምቀት በቅዱሳ ታሪክ እና ሕዝብ በእምነትን የሚገልጠው መንፈሳዊነት የኤውሮጳ ባህል የክርስትና መሠረት ያለው መሆኑ የሚመስክረው ሓቅ በኤውሮጳ ወንጌል አብሣሪነቱን ብቻ የሚገለጥ ሳይሆን፣ በኤውሮጳው ባህል ሰርጾ ያለው የሕይወት ምንጭ የሆነውን ወንጌል ጠለቅ ብሎ ማጤን እስፈላጊ መሆኑ ይህ ያንድ ሺሕኛው የፔክስ ቁምስና ምሥረታ ያሳሰበዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.