2009-08-24 14:18:44

የስደተኞች መብት እና ፈቃድ ማክበር


የስደተኞች እና የተጓዦች ሓዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በቅርቡ ወደ ኤውሮጳ ለመሰደድ ከሊቢያ በትንሽ መርክበ ተነስተው ይጓዙ በነበሩት የሕገ ወጥ ስደተኞች ላይ RealAudioMP3 የደረሰው አሰቃቂው የሞት አደጋ አስመልከተው ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16 ፍቅር በሐቅ በተሰየመው አዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት፣ “ማናኛው ስደተኛ ሰብአዊ ፍጡር መሆኑና በማንኛው ወቅት እና ሁኔታ የሚከበር ፈጽሞ የማይታበል መሠረታዊ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ባለቤት ነው” ያሉትን ሃሳብ አስታውሰው፣ ወደ ተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ለመግባት ሜክሲኮ ከተባበሩት የአሜሪካ መግንሥታት ጋር በሚያዋስነው ድንበር፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በጠቅላላ ካፍሪቃ ካለው ከተለያየ ማህበራዊ ሰብአዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያው መሠረት ካላቸው ችግሮች ለመላቀቅ ሕዝቦች በሚከናውኑት የስደት ጉዞ የሚያጋጥማቸው የሞት አደጋ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ በቸልታ ሊያየው አይገባም ብለዋል።

የድኾች አገሮች ሕዝብ ዘርፈ ብዙ ችግርችን አርቆ በሚያስብ ዘላቂነት ባለው ልባም የትብብር እና የድጋፍ ፖሊቲካዊ እቅድ አማካኝነት ሊፈታ እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን በአዋዲ መልእክታቸው ዘንድ ያቀረቡት ጥሪ ብፁዕ አቡነ ቨሊዮ በመጥቀስ ስደተኛ እንደ ማንኛው ሰብአዊ ፍጡር ሊከበርና ችግሩ ተደምጦ መፍትሔ ማግኘት ይኖርበታል፣ በርህን በመዝጋት ለተለያዩ ችግሮች ማጋለጥ ግን ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው ብለዋል። የስደተኛው እና የስደተኛው ቤተ ሰብ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ለማክበር እንዲቻል ኵላዊነት ያለው ፖለቲካዊ አግባብ ማረጋገጥ የሁሉም መንግሥታት ኃላፊነት ነው ካሉ በኋላ እ.ኤ.አ. ከ 1988 ዓ.ም. ወዲህ ለመሰደድ በሚደረገው ጉዞ የሞት አደጋ ያጋጠመው ህዝብ ብዛት 14 ሺሕ 660 መሆኑም በቅርቡ ስለ ስደተኛ ጉዳይ በተመለከተ የቀረበው አኃዛዊ የጥናታዊ ሰነድ በመጥቀስ በተለያዩ ችግሮ ተገፋፍተው እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማዳን ለሚሰደዱት ሁሉ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ተከብሮላቸው ከለላ እና ተገቢ መስተንግዶ ማግኘት ይኖርባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.