2009-08-24 16:32:57

የር.ሊ.ጳ የጸሎተ መልኣከ እግዚኣብሔር ኣስተምህሮ


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ. በ. 16ኛ ትናንት እሁድ ለበጋ ዕረፍት ከሚገኙት ከካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ አዳራሽ አጥር ግቢ የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት አስተምህሮ አቅርበዋል።
ለዛሬ አስተምህሮ እንደ መግቢያ የተጠቀሙት ከአንድ ወር በፊት አንዳልጠው እጃቸውን ከተጐዱ በኋላ በሕክምና ወጌሻዎች ሲያክምዋቸው ያደጉላቸው ፋሻና ጀሶ በማለቃቃቸው ደስ ብሎዋቸው፣ ‘ተመልከቱ፣ እጄ ከጀሶ ነጻ ሆነዋል፣ ግን ገና ትንሽ ግዜ ስለሚያስፈልጋት በትዕግሥት ትምህርት ቤት መቆየትየ ነው፣’ ሲሉ እጃቸውን አወዛውዘው ካሳዩ፣ ያህ ሆነ ይህ ወደ ዛሬው አስተምህሮ እንመለስ አሉና፣ የሚከተለውን አቅርበዋል።

ወደ ዋና አስተምህሮአቸው በመመለስ፣ በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ከባለፈው ወር የእሁድ ቃለ እግዚአብሔር በወንጌል ዮሓንስ ምዕራፍ 6 ላይ ያቶኰረ መሆኑን አስታውሰዋል፣ በዚህ ምዕራፍ ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ ኅብስተ ሕይወት መሆኑ ለማስተማር ‘‘ከሰማይ የወረደው ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፣ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል፣ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን እኔ የምሰጠው እንጀራ ሥጋየ ነው።’’ ባለ ጊዜ አይዳውያን፣ ‘’ይህ ሰው ሥጋውን እንድንበላ እንዴት ሊሰጠን ይችላል? ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ።

አሁንም ቢሆን ዓለማችን ገና በዚህ ጉዳይ ላይ እየተጠራጠረና እየተከራከረ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ግን ዛሬም ‘’እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።’’ ይላል።

ይህ አጋጣሚ እኛስ ይህንን መልእክት በእውነት ተረድተነዋልን? ብለን ለማስተንተን ይጠቅመናል።

በዛሬው እሁድ የምዕራፉን መጠቃለያ ሓሳብ እናስተንትናለን፣ ወንጌላዊው ዮሓንስ የኢየሱስ ስለ እውነተኛ ምግብ የሆነው ሥጋውና ስለ እውነተኛ መጠጥ የሆነው ደሙ ሲናገር የሰሙ አይሁዶች፣ ደቀ መዛሙርቱም ሳይቀሩ ግራ እንደገቡና ይህ ንግግር ዕንቅፋት እንደሆነባቸው ይተርካል። ከፊሎቹ እስከ እዛች ሰዓት ተከትለውት ይህንን ንግግር በተናገረ ጊዜ ‘’ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?’’ አሉ። ከዛ ግዜም በዚህ የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።

በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥም ልክ እንዲህ ዓይነት ክህደትና እምነት ወደ ኋላ ማፈግፈግና ወደ ፊት መገስገስ ሁል ጊዜ ሲያጋጥም ኖረዋል። ኢየሱስ ሁኔታውን ለመሻሻል ወይም ለአድርባይነት ወይም ተከታዮችን ላለመክሰር እንዲግባባና ትብብር እንዲጠይቅ ሊጠበቅ ይችላል፣ ሆኖም ግን ኢየሱስ በተናገረው ድርቅ ብሎ ይቀራል፣ የባሰውኑ ወደ 12 ሓዋርያት መለስ ብሎ ‘’እናንተስ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ።

ይህ ቀስቃሽና ውሳኔ ለመውሰድ የሚያነሳሳ ጥያቄ ያኔ ሲያዳምጡት ለነበሩ ለነዛ ሰዎች ብቻ ኣይደለም፣ ይህ ዘለዓለማዊ ቃል ለሁል ጊዜ በመሆኑ ለሁሉም ዘመን የእርሱ ተከታዮች ምእመናንና በሁሉም የሰው ልጆች ዘመን ሲያስተጋባ የሚኖር ዘለዓለማዊ ቃል ነው።

ዛሬም ይህ የክርስትያን እምነት ተጻጻሪ መልእክት ዕንቅፋት የሚሆንባቸው ጥቂት አይደሉም። የኢየሱስ ትምህርት ለመቀበሉ ከባድ ይመስላል፣ እተግባር ላይ ማዋሉም እጅግ የሚስያስቸግር ይመስላል። በዚህም ምክንያት ክርስቶስን የማይቀበልና ጥሎት የሚሄድ ብዙ ሰው አለ፣ ቃለ ወንጌሉን ለራሳቸው በሚመች ሁኔታ በመተርጐም መልእክቱና ይዘቱን በመጠምዘዝ እንዳሻቸው የሚኖሩም ጥቂቶች አይደሉም።

‘’እናንተስ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? የሚለው ቃል ዛሬም በእያንዳንዳችን ጆሮና ልብ እያስተጋባ፣ ከእያንዳንዳችን ቍርጠኛ መልስ ይጠብቃል። ለእያንዳንዳችን የሚቀርብ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ኢየሱስ በአፍ ወለምታ ብቻ የሚደሰት አይደለም፣ ተግባር የሌለበት የለይስሙላ አባልነት አድርባይነት ወይም ክርስትያን ነኝ ብሎ መመስከር ለእርሱ በቂ አይደለም። ቍርጠኛ ውሳኔ በማድረግ በሕይወት ዘመን ሁሉ ለእርሱና በእርሱ መኖርን ይጠይቃል። ኢየሱስን መከተል ልባችንን በደስታ ይሞላል፣ ለሕይወታችን ትርጉም ይሰጣል፣ ሁል ጊዜ ቅራኔና ፈተና ስላለ ይህ ጉዞ ቀላል አይደለም።

‘’እናንተስ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? ለሚለው የኢየሱስ ጥያቄ ሐዋርያት ሁሉንና የዘመናት ሁሉ ምእመናንን ወክሎ ቅዱስ ጴጥሮስ፦‘’ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

ውድ ውንድሞቼና እኅቶቼ፤ ሰብአዊ ድካማችንና ያለንን ችግርንና ፈተናን ብናውቅም ቅሉ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን በመቀበል ከኢየኡስ ጋር አንድ በመሆን በሚገለጸው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመተማመን እኛም በዚህች ሰዓት ይህንን የቅዱስ ጴጥሮስ መልስ ለመድገም እንችላለን።

እምነት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚሰጠው ጸጋ ነው፣ ይሁን እንጂ ይህ ስጦታ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ያለውን ነጻና ለበ መሉ መተማመንንም ያካትታል። እምነት በትሕትና ‘እንደ መብራት የሚመራንና፣ ለመንገዳችንም ብርሃን ለሆነው’ የእግዚአብሔር ቃልን ማዳመጥ ነው።

ልባችንን በእምነት ለኢየኡስ የከፈትንና እርሱ ሕይወታችን እንዲገዛና እንዲመራ የፈቀድንለት እንደሆነ፣ የአርስ ቆሞስ ቅዱስ ዮሓንስ ማርያ ቫያነ እንዳለው ‘በዚች ምድር አንድዋና ብቸኛዋ ደስታችን እግዚአብሔርን ማፍቀርና እርሱ እንደሚይፈቅረን ማወቅ ነው’ ያለውን እያጣጣሙ መኖር ነው።

የአምላክ እናትና የምእመናን ሁሉ እናትና አብነት ለሆነችው እመቤታችን ድንል ማርያም ይህንን በፍቅር የሞላ እምነትን በልባችን እንድታኖርልን እንለምናት፣ ብለው የመልአከ እግዚአብሔርን ጸሎት አሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ በዕለቱ ‘በሕዝብ መካከል ጓደኝነት እንዲሰፍን ለሚደረገው በሪሚኒ 30ኛው ለተሰበሰቡ ጉባኤኞች በቀጥታ ብተለቪዥን የተላለፈ ሰላምታና መልእክት አስተላፈዋል፣ በካሪታስ ኢን ቨሪታተ ባሰፈሩት መልእክት መሠረት የጉብኤው ተሳታፊዎች ‘ዕውቀት ቍሳዊ ብቻ አለመሆኑን እንዲረዱና በእያንዳንዱ ዕውቀትና በእያንዳንዱ የፍቅር ተግባር የሰው ልጅ ነፍስ ከእግዚአብሔር የተቀበለችውን የዕውቀት ሥጦታና ከፍታ የሚያጣጣም ጸጋ መሆኑን የሚያስገንዝብ’ ጉባኤ እንዲሆንላቸው በመመኘት አጋርነታቸውን ገልጠዋል።

በመጨረሻም ከተለያዩ ቦታዎች ለመልእከ እግዚኣብሔር ጸሎት ለተሰበሰቡት በተለያዩ ቋንቋዎች ኣመስግነው በሥርዓቱ ለተገኙት ምእመናን ሓዋርያ ቡራኬና ሰላምታ ኣቅርበው ኣሰናበቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.