2009-08-24 14:25:27

በስታሊን እና በናዚ ፖለቲካዊ ሥርዓት ለሞት የተዳረጉትን መዘከር


በኤውሮጳ በስታሊንዝም እና በናሲዝም የወደቁት፣ ለሞት የተዳረጉት ዜጎች የሚዘከሩበት እለት ቀደም ተብሎ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ትላትና የመጀመሪያው ዝክረ ዕለት ተፈጽሟል። የዛሬ 70 ዓመት በፊት በቀድሞ ሶቪየት ህብረት RealAudioMP3 እና በጀርመን የናዚ መንግሥት መካከል ምንም ዓይነት ጦርነት እና ግጭት እንዳይከሰት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 23 ቀን 1929 ዓ..ም. የተደረገውን ስምምነት ቀን በስታሊን እና በናዚው ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት የወደቁት የሚዘከሩበት እለት እንዲሆን የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው ሀሳብ ከትላንትና ጀምሮ ገቢራዊ መሆን ሆነዋል። ቀኑን መክንያት በማድረግ ቶሪኖ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የታሪክ እና ያለም ዓቀፍ ስነ ግኑኝነት ጉዳይ መምህር የታሪክ ሊቅ ኤኒዮ ዲ ኖልፎ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሁለት ዓይነት የፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት እርሱም የፋሺስት እና የናዚ መንግሥት ሥርዓት ጨርሶ እንዲወገድ ሲያደርግ፣ በሌላው ረገድ ግን የስታሊኒዝም ሥርዓት እንዲያይል ያደረገ አጋጣሚ መሆኑ ጠቅሰው፣ ይህ አይነቱ የኮሙኒዝም ሥርዓት ተከስቶ እንዲያያል ያደረገ የታሪክ አጋጣሚ ነው። የኮሙኒዝም ሥርዓት በአሁኑ ወቅት የለም ቢባልም’ኳ ባንዳንድ አገሮች የሥሮኣቱ ተጽእኖ ያለባቸው መንግሥታት እንዳሉ የማይካድ ነው ብለዋል። የኤውሮጳ ኅብረት ምሥረታ ምክንያት አንዱ በኤውሮጳ ክልል አገሮች ተመሳሳይ የታሪክ ስህተት እንዳከሰት ዋስትና ለመስጠት ሲሆን፣ በኤውሮጳ የፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት የሚያንጸባርቅ የፖለቲካ ጽንሰ ሀሳብ የለም ቢባልም’ኳ ስውር የፖሊቲካ ፍላጎት ሆኖ ባንዳንድ አጋጣሚ በተዘዋዋሪ ሲገለጥ እና በዴሞክራሲይው ሥርዓት ከለላ ያንድ የፖለቲካ ሰልፍ አመለካከት ሆኖ ዳግም ሊወለድ ይችላል፣ ስለዚህ በተለያዩ የፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት የወደቁትን መዘከር ይህ ዓይነት ጸረ የሰው ዘር የሆነው መንግሥት ዳግም እንዳይክሰት በፈላጭ ቆራጭ መንሥታት ዘንድ የተፈጸመው የሰው ዘር እልቂት ህያው ሆኖ መዘከር እና ታሪኩ ለትውልድ ማስተላለፍ ለሰላም ዋስትና ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.