2009-08-21 14:13:21

ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት


ዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት እና ተልእኮአቸውን ያጠናቀቁት ቄስ ሳሙኤል ኮቢያ ዳግም ለመመረጥ እንደማይሹ በማሳወቃቸው ምክንያት እሳቸውን የሚተካ ለመምረጥ ምክር ቤቱ RealAudioMP3 በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ተገልጠዋል። ቄስ ኮቢያን ለመተክት በእጩነት የቀረቡት የደቡባዊት ኮሪየ የፕረስቢተሪያን ቤተ ክርስትያን አባል ቄስ ፓርክ ሴኦንግዎን እና የኖርወይ ሉተራን ቤተ ክርስያን ቄስ ኦላቭ ፍይክሰ ትቫይት መሆናቸው ተገልጠዋል።

የዚህ ዋና ጽ/ቤቱ ጀነቭ የሚገኘው ዓለም አቀፍ ያቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት በዋና ጸሓፊነት ለመምራት እጩ ሆነው የቀረቡት የደቡብ ኮሪያ ዜጋ ቄስ ፓርክ ሴኦንግዎን በዩንግናም እና በፕረስቢተሪያን የመጋቢያን ተማሪዎች የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር የቲዮሊግያ ሊቅ የዚህ የዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት አባል ከዚህ ቀደም የተሃድሶ ፖርተስታን አቢያተ ክርስትያናት ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ሁለተኛው እጩ የኖርወይ ዜጋ ቄስ ትቫይት በዚህ የዓለም አቀፍ ያቢያተ ክርስትያናት ምክር ቤት የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ እና የምክር ቤቱ የእምነት ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት አባል በመሆን እያገለገሉ መሆናቸውም ሲነገር፣ የዚህ የዓለም አቀፍ የአቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት አለ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአባልነት የኦርቶዶክስ የአንግሊካን እና የፕሮተስታትን አቢያተ ክርስትያን በጠቅላላ 347 አቢያተ ክርስትያን ያቀፈ መሆኑም የሚታወቅ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.