2009-08-21 14:11:39

ሜክሲኮ፣ ጸረ ውሉደ ክህነት አመጽ


በሜክሲኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት ወር 2003 ዓ.ም. በጓዳላካራ ያየር ማረፊያ እንደደረሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ለሞት የተዳረጉት የጓዳላካራ ሰበካል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኹዋን ኼሱስ ፖሳዳስ ኦካምፖ የሚገኙባቸው RealAudioMP3 እ.ኤ.አ ከ 1993 ዓ.ም. ወዲህ 11 ካህናት እና 4 ገዳማውያን በአመጸኞች እጅ መገደላቸው የሜክሲኮ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት “የካህናት መሰደድ በሜክሲኮ” በሚል ርእስ ሥር ካወጣው ሰነድ ለመረዳት ተችለዋል።

ሰነዱ እንደሚያመለክተውም በዚህች አገር ካህናት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ደናግል ገዳማውያን ለአደጋ እና ለአመጽ የተጋለጡ መሆናቸው ሲነገር፣ በተለይ ደግሞ በጉአረሮ በቻፓስ እና በኣክሳቻ የወንጀል ብድኖች አማካኝነት ቤተ ክርስትያን እና አባላቷ ላደጋ የተጋለጡበት መጋለጣቸው ሲገለጥ፣ ያደንዛዥ ዕጸዋት ንግድ፣ ሰዎችን በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ በሚያንቀሳቅሱ የወንጀል ቡድኖችን በመቃወም እና የሚፈጽሙት በደል የሜክሲኮ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ድምጿን ከፍ በማድረግ በማውገዝ የሰው ልጅ ክብር የሚሰርዝ ሁሉ የሞት ባህል መሆኑም በማስተማር ጸጥታ እና ደህንነት እንዲረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች የምትሰጠው አስተምህሮ ላደጋ ያጋለጣት ቢሆም ቅሉ፣ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ከማብሰር እውነተኛው ነጻነት ከማስተማር፣ የተሟላ ሰብአዊ እድገት እንዲረጋገጥ ካለ መታከት ስብከተ ወንጌል እና የህንጸት መርሃ ግብር ከማረጋገጥ እንደማትቦዝን ሰነዱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.