2009-08-19 13:47:19

ውህደት እና ነጻነት


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ሮማ ሪሚኒ ከተማ 30ኛው የኮሙኒዮነ ኤ ሊበራዚዮነ፣ ውህደት እና ነጻነት የተሰኘው የካቶሊክ ማኅብር ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የአውደ ጥናት ጉባኤው እንደሚያካሂድ ተገለጠ።RealAudioMP3 ይህ “እውቀት ዘወትር ድርጊት/ሁኔታ ነው” በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ ላንድ ሳምንት የሚካሄደው 30ኛው ጉባኤ በተመለከተ ባለፈው ግንቦት ወር በ RealAudioMP3 ፓሪስ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበባትና የባህል ድርጅት ዋና ጽ/ቤት በሚገኘው የማስታወቂያና የህትመት ክፍል በይፋ መገልጫ እንደተሰጠበት የሚዝከር ሲሆን፣ የጉባኤው ቅድመ ዝግጅት ስብሰባዎች በብራዚል በሚገኘው በኢጣሊያ ልኡከ መንግሥት ጽ/ቤት፣ በኢጣሊያ በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ልኡክ ጽ/ቤት መከናወኑም ለማወቅ ተችለዋል።

ስለዚህ እፊታችን እሁድ በይፋ ስለ ሚጀመረው የኮሙኒዮነ ኤ ሊበራዚዮን ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት በተመለከተ የኮሙኒዮነ ኤ ሊበራዚዮነ ያመታዊ ዓውደ ጥናት የሚከታተለው ንኡስ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ የካቶሊክ ማኅበር ስብሰባው የዛሬ ሰላሳ ዓመት በፊት አንድ ብሎ ሲጀመር እዚህ ይደርሳል ተብሎ ቀድሞ ያልታሰበ ቢመልስም’ኳ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ምንም ነገር ሳያግደው ይኸው 30ኛውን ዓመታዊው ጉባኤውን ለማካሄድ በቅተዋል።

ፍላጎታችን እና እርካታችን ብሎም ማረፊያችን ለመፈለግ በዚህች አለም የምናደርገው ውጣ ውረድ ሁሉ ሸኝ እንጂ ግብ አይደለም፣ ሁሉም መሸጋገሪያ ነው፣ ለዚህም ነው ደግድሞ እውቀት ሁኔታ ነው የተባለበት ምክንያት፣ በእለታዊ ኑሮአችን አማካኝነት ልባችን ሕይወታችን የሚሻው መድረሻ ለይተን ስናውቅ እወቀቱ ሁኔታ መሆኑ እንረዳለን ካሉ በኋላ ዘንድሮ የሚካሄደው ዓውደ ጥናት በስነ ቅብ ትርኢት፣ በተለያዩ ላቲን አሜሪካ አገሮችን የሚያንጸባርቁ የባህላዊ ስነ ቅብ ትርኢት በመዝሙር ኮንሰርት የተሸኘም እንደሚሆን አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.