2009-08-19 13:42:22

በኢጣሊያ፣ አዲሱ የስደተኛ መተዳደሪያ ሕግ


በኢጣሊያ መንግሥት ያጸደቀው አዲሱ የስደተኛ የመተዳደሪያ ሕግ ገቢራዊ መሆን በጀመረበት ሳምንት የስደተኛው ሠራተኛ እና የስደተኛው ቤተ ሰብ እለታዊ ኑሮ እና ወቅታዊው ሁኔታ እጅግ እየነካ መሆኑ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 አዲስ ሕግ በስደተኛው ላይ እያስከተለው ያለው ተጽእኖ በማስመልከት የቺስል በመባል ለሚጠራው የሠራተኞች ማኅበር የስደተኛ ሠራተኛ ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ የፐሩ ዜጋ ሊሊያና ኦክሚን ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የስደተኛው ሠራተኛ መብት እና የስደተኛው ቤተ ሰብ መብት ዋስትና መስጠት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው ብለዋል።

ሊሊያና ኦክሚን አዲሱ የስደተኛው መተዳደሪያው ደንብ አለ መኖሪያ ፈቃድ ነገር ግን አለ ሕግ ተቀጥረው ለሚሠሩት ሕገ ወጥ ስደተኞች ችግር የሚያስከትል እና በሕጉ አንጻርም ሕገ ወጥ ስደተኛ ወንጀል በመሆኑ ምክንያት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት የሚታይ ሆነዋል፣ ስለዚህ የስደተኛው ጉዳይ እጅግ እየተወሳሰበ ነው ብለዋል። ብዙ ስደተኛ ሥራ እያለው ነገር ግን በአሠሪው ውሳኔ መሠረት አለ ሕግ እንዲሠራ ተገዶ ሥራ አለኝ ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ ለመጠየቅ እንዳይነሳ አግዶታል፣ ስለዚህ አሠሪው ተቀጣሪው ስደተኛው ሕጋዊ ሠራተኝ እንዲሆን ለማድረግ በሕግ አማካኝነት ግዴታ አለባቸው፣ ካሉ በኋላ ያም ሆኖ ይህ አዲሱ የስደተኛ የመተዳደሪያ ደንብ መሻሻል ይኖርበታል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.