2009-08-19 13:49:33

ሱዳን


የተባበርት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት አገሮች ማኅበር እንዲሁም የሱዳን የፍትሕ እና የእኩልነት ንቅናቄ በዳርፉር የሰላም ስምምነት እቅድ ማረጋገጥ በሚል ዋና ርእሰ ሥር በተደረገው ውይይት የዜጎች ሰብአዊ መብት፣ RealAudioMP3 አገርን መቆጣጣር በተሰኙት አንገብጋቢ ጥያቂዎች በማስደገፍ ሰፊ ውይይት መካሄዱ የአፍሪካ ህብረት ለዳርፉር ጉዳይ ልኡክ ከሱዳኑ የፍትሕና የእኵልነት ንቅናቄ መሪ ክሃሊል ኢብራሒም ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መገልጫ አስታውቀዋል።

የዚህ ጄም በመባል የሚጠራው የሱዳን የፍትሕና የእኵልነት ንቅናቄ መሪ ክሃሊል ኢብራሒም ባለፈው ሳምነት ከተባበሩት መንግሥታት ለዳርፉር ልኡክ ጋር መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ እነዚህ የተካሄዱት ግኑኝነቶች መስከረም ወር 2009 ዓ.ም. በካርቱም መንግሥት እና በዚህ ጄም ንቅናቄ መካከል በቀጠር የሚካሄደው የሰላም ድርድር ያስቀደሙ ግኑኝነቶች መሆናቸውም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.