2009-08-17 14:30:42

አፍሪካ ትጠራናለች


እ.ኤ.አ. ከነሓሰ 23 ቀን እስከ መስከረም 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ስለ አፍሪካ ጉዳይ የሚወያይ የባህል አውደ ጥናት በኢጣሊያ ፓርማ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጠዋል። ይህ ካፍሪካ ጋር አብረን እንራመድ በሚል ርእስ ሥር RealAudioMP3 የሚመራው ስለ አፍሪካ ጉዳይ በተለያዩ ዘርፎች ተንተርሶ እርሱም በህንጸት እና በሥራ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ፓርማ በሚገኘው የግብረ ተልእኮ ወንድማማችነት ማኅበር ዋና ህንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እንደሚፈጸመ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ዓውደ ጥናቱን ያዘጋጀው አፍሪካ ኪያማ አፍሪካ ትጣራለች የተሰኘው ስለ አፍሪካ ጉዳይ የሚንከባከበው የግብረ ሰናይ ማህበር እና እንዲሁም አፍሪካን ማበርታት የተሰኘው የግብረ ሰናይ ማኅበር መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ ስለ አፍሪካ ጉዳይ በሚወያየው ዓውደ ጥናት በእንግድነት ስለ የቤኒን ሴቶች ሁኔታ የሚተርክ መጽሓፍ የደረሱት እና ባፍሪካ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽ በሁሉም መድረክ በጥናታዊ ሰነድ የተደገፈ መራጃ በማቅረብ ስለ ሴቶች መብትና ፈቃድ መከበር ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ኢሲልከ ኢክፒታንይ እንደሚገኙም ሚስና የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.