2009-08-14 13:04:08

የፍቅር ተግባር ካቶሊክ ወጣቶች ማኅበር


የፍቅር ተግባር የተሰኘው የካቶሊክ ወጣቶች ማኅበር እስከ እፊታችን እሁድ የሚቆየው 18ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤውን ትላትና በይፋ ጀምረዋል። ይህ ከጠቅላላ የኤውሮጳ አገሮች የተወጣጡ የማኅበሩ አባላትን የሚያሳትፈው ዓመታዊ ጉባኤ፣ RealAudioMP3 መሠረታዊ የሕይወት እሰይታና የክርስትናው እምነት በጸሎት በአስተንትኖ በትምህርተ ክርስቶስ በምስክርነት እና በመንፈሳዊ የሙዚቃ ኮንሰርት አማካኝነት የሚመሰከርበት አጋጣሚ እንደሚሆንም የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሊኖ ኤውፓኒ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ ማኅበሩ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም መፈሳዊነትን እና እምነትን በጥልቀት በመረዳት በመኖር እንዲመሰክር የሚያነቃቃው ሲሆን ዋናው መንፈሳዊ ዓላማው እንደ ማርያም የሚል መሆኑ ገልጠዋል።

ይህ ወጣቱ የማርያምን በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ሚና ለይቶ በመረዳት እምነቱን በዘልማድ ሳይሆን ባድናቆት ይኖረው ዘንድ በጠቅላላ በእምነት ተደጋግፎ ከቤተ ክርስትያንና በተለይ ደግሞ በቤተ ክርስታን ሥር ክርስቶስን ለመኖር ብሎም ለማብሠርን የሚያነቃቃ ሲሆን፣ የዘንድሮው ጉባኤው “የተስፋ ምስክር እናት ሆይ ሁሉም ያንቺ ናቸው” በሚል መርኅ የሚሸኝ መሆኑም ኤውፓኒ አስታውቀው፣ ዘወትር የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መሪ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ታማኝ አገልጋዮች በመሆን፣ የማርያም ጥልቅ መንፈሳዊነት አማካኝነት እምነትን ማጎልበት የዛለውን እምነት ዳግም ለማነቃቃት በያመቱ የሚከናወን ጉባኤ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.