2009-08-14 13:07:27

የዓቢይ ሓይቅ ክልል አገሮች ወጣቶች እለት


የዓቢይ ሓይቅ ክልል አገሮች ካቶሊክ ወጣቶች እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 29 ቀን እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በቡሩንዲ ርእሰ ከተማ ቡጁምቡራ አንደኛው ክልላዊ የወጣቶች ቀን RealAudioMP3 ማክበራቸው ተገለጠ።

ከብሩንዲ ከሩዋንዳ ከዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ የተወጣጡ ካቶሊክ ወጣቶች በጋራ በመገናኘት ለሰላም ባህል በጋራ እንዲጠመዱ የሚያግዝ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑም ሲነገር፣ ይህ የወጣቶች ቀን እንዲከበር ቀድሞ ዝግጅቱን የተከታተሉት የጂቴጋ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሲሞን ንታምዋና ባላቸው የመካከለኛ አፍሪካ አገሮች የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማኅበር የሊቀ መንበርነት ኃላፊነት መሠረትም በነዚህ የአቢይ ሓይቅ አገሮች ሓዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳችው እና እርቅ ሰላም ይቀር መባባል በጠቅላላ ክርስትያናዊ እሰይታዎች በወጣቱ ሕይወት ዘንድ ጎልቶ ለዚህ ክልል ሰላም ቀዳሚ ተወናያን እንዲሆሉ ለማገዝ ያቀደ እምደሚሆን ከግኑኝነት በፊት ቀድመው በሰጡት መግለጫ አስታውቀው እንደነበርም የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.