2009-08-14 15:11:45

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲቶስ መልእክት ለፐክስ ሀገረ ስብከት.


በምሥራቅ ኤውሮጳ የሀንጋሪ ፐክስ ሀገረ ስብከት የተመስረተበት ሺሐኛ ዓመት በማክበር ላይ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ለዚሁ ዝክረ ዓመት መልእክት እንደላኩ የቅድስት መነበር መግለጫ አስታወዋል።

የፐክስ ሀገረ ስብከት ዝክረ በዓል ምእመናን እምነታቸው እንድያሳድሱ ልቅዱስ መጽሐፍ እና ቤተክርስትያን ያላቸውን ፍቅር የሚያሳድሱበት ግዜ መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለሀገረ ስብከቱ ጳጳሳት የላኩት መልእክት እንደሚያመለክት መግለጫው አመልክተዋል ።

በአውስትርያ የቪን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ክሪስቶቭ ሾንቦርን በዚሁ ፊታችን ሰንበት በሃንጋሪ ፐክስ ሀገረ ስብከት ተዘክሮ እና ተከብሮ በሚውለው የምሥረታ ሺሕኛ ዓመት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስን እንዲወክሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደሰየምዋቸው የቫቲካን መግለጫ አስረድይተዋል ።

የሀንጋሪ ፐክስ ሀገረ ስብከት በርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሰርጂዮ አራተኛ የአምስት አብያተ ክርስትያናት ሀገረ ስብከት ትጠራ መኖርዋ ተወስተዋል።

ይሁን እና የፕክስ ሀገረ ስብከት ሺሐኛ ዓመት ምሥረታ የኤውሮጳ ጥንታዊ ክርስትና የሚያስታውስ መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለዝክረ ዓመቱ ወደ ሀንጋሪ የላኩት መልእክት መግለጡም መግለጫው ገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው እንደጀመሩ ወድያውኑ የኤውሮጳ ህዝቦች መሠረታዊ ታሪካቸው እና ባህላቸው የሆነ ክርስትና እንዳይዘነጉ ደጋግመው መግለጣቸው የሚታወስ ነው።

ሕብረት ኤውሮጳ ለመገንባት እና የበለጸገች ኤውሮጳ ክርስትና ላይ የተመረኰሰች ትሆን ዘንድ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጸቻውም የማይዘነጋ ነው ።

አለ ሐቀኛ ታሪክ ብሩህ መጻኢ ሊኖር እንደማይችል ከኤውሮጳ ጳሳት ጋር በተገናኙበት ግዜ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ምስራቁ ኤውሮጳ በማስታወስም ከከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ርቀው የኖሩ ሀገራት ያጋጠማቸው ውጥንቅጥ ራሱ እንደሚመሰክር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ማስታወሳቸው የሚዘከር ነው ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ክርስትና የኤውሮጳ ማንነት ታሪክ እና ባህል መሆኑ ከተመሰረተች ሺሐኛ ዓመት በማክበር ላይ የምትገኛው በሀንጋሪ ለየስፐክ ሀገረ ስብከት የላኩት የዝክረ ዓመት እና ደስታ መግለጫ እንደሚያመላክት ከቫቲካን የወጣ መገልጫ አስገንዝነዋል።

እንደሚታወሰው በ2007 መስከረም ወር ላይ እኤአ አውስትርያ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ግዜ በማርያጸል ገዳም ኤውሮጳ ፊትዋ ወደ ክርስቶስ መመለስ ይጠበቅባታል ብለው መኖራቸው የሚታወስ ነው ።

የኤውሮጳ ባህል በጸሎት እና ስራ ላይ የተመረኰሰ ጥንታዊ ባህል መሆኑ ቅዱስ አባታቻን ከማስታወስ እንዳልቀሩ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ ያስታውሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.