2009-08-14 13:02:54

የሕክምና አገልግሎት ለሁሉም


የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የአገሪቱ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ሥርዓትና መመሪያ እንዲሻሻል በተለይ ደግሞ ሕክምና የዜጎች መብት ነው ከሚለው አመለካከት በመነሳት አገልግሎቱ ለሁሉም ለማደስ RealAudioMP3 የርእሰ ብሔር ኦባማ መንግሥት ያቀረበው ሐሳብ፣ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሚደገፈው መሆኑ በማሳወቅ፣ ነገር ግን ጽንስ የማስወረዱ ጸረ ሕይወት ተግባር የሚያነቃቃ መሆን እንደሌለበት፣ በፊላደልፊያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጁስቲኒ ሪጋሊ አማካኝነት ባስተላለፈው መልእክት አስገንዝበዋል።

ይህ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በምክር ቤት ስለ ሕይወት የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ሪጋሊ በኩል ያስተላለፈው መልእክት፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚተዳደሩት እና ድኾች ያገሪቱ ዜጎች የሕክምና አገልግሎት ከማግኘት መብት የተገለሉ እንዳይሆኑ የአገሪቱ መንግሥት የሕክምና መስጫ አገልግሎት መመሪያ ለማሻሻል ወጥኖት ያለው ደንብ የሚደገፍ መሆኑ በማሳወቅ፣ ሆኖም ግን ማንኛውም ጸረ ሕይወት የሆነ ተግባር የማያነቃቃ መሆን እንደማይገባው ማሳሰብ ታውቀዋል።

ዜጎች የሚከፍሉት የሕይወት መድኅን ዋስትና የተሟላ ሕክምና ለማግኘት የሚፈሰው ወጪ የማይሸፍን በመሆኑ፣ ከዚህ አኳያ የተሟላ ሕክምና ከማግኘት የተገለሉትን አስቦ ሕክምና ለሁሉም ለማዳረስ ያቀደው የመንግሥት አዲስ የሕክምና አገልግሎት መተዳደሪያ ደንብ ንድፍ የሚደገፍ ነው፣ ሆኖም ጽንስ ለማስወረድ የሚገፋፋ መሆን እንደሌለበት የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መልእክት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.