2009-08-14 16:32:28

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ነጋድያን ሳምንት በፋጢማ ቤተ መቅደስ


የፖርቶ አለግረ ረዳት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኣለሳንድሮ ካርመሎ ሩፊኖኒ ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ነጋድያን ሳምንት በፋጢማ ቤተ መቅደስ መምራታቸው ተመለከተ። በፖርቱጋል ደብረ ፋጢማ በየዓመቱ የሚፈጸም የዘንድሮ የስደተኞት ነጋድያን ሳምንት ነገ ቅዳሜ ይፈጸማል።

ብፁዕ አቡነ ኣለሳንድሮ ካርመሎ ሩፊኖኒ የንግደቱን ትርጉም እንዲገልጹ በቫቲካን ረድዮ ባልደረባ ተጠይቀው ሲመልሱ፦ ‘‘ይህ ሳምንት የጸሎት የግኑኝነትና የውይይት ሳ ምንት ነው። የሳምንቱ መዝጊያ ቅዳሴ እኩለ ሌሊት ላይ ያርጋል፣ በመጨረሻም ሕዝቡ ቀንዴልና ሻማ ይዞ እየዘመረ የእመቤታችን ዑደት ያካሄዳል ጸሎተ መቍጠርያም ያሳርጋል። የዘንድሮው ንግደት የእግዚአብሔር አገልጋይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ 23ኛን ትዝ እንዲለኝ አደረገ፣ ቅዱስነታቸው ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤን ሲከፍቱ ብተመስጦ እንዲህ ብለው ነበር፣ ‘ተመልከቱ የዚህን ያህል ሕዝብ እምነት ትዕይንት ጨረቃም የምታደንቀው ይመስላል’’ ያኔ ከመንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስትያን መሪነትና ጉባኤ ብርሃን ለመለመን ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ነበር። ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ያኔም ይሁን አሁን ቤተ ክርስትያን ለዓለም የተከሠተችበት ነው። ዛሬም ያንን የእምነት ተግባር መድገም ፈልገናል፣ እነዚህ ትናንሽ የሻማ ብርሃኖች እያንዳንዱ ክርስትያን በልቡ የያዘውን የእምነት ብርሃን ያመልክታሉ፣ ትልቁ ብርሃን ደግሞ ኢየሱስ ነው።’’ ካሉ ብኋላ ዛሬ ምን ዓይነት ምስክርነት ሊሰጡ እንደሚፈልጉ ተጠይቀው ሲመልሱ፣ ‘‘እኛ ለዚህ ገና የኢየሱስ ፍላጎት ላለው ዓለም ኢየሱስን ለመስጠት እንፈልጋለን። ዮሐንስ ባቲስታ እስካላብሪኒ እንዳለው ‘እነኚህ ፈላስያን በእግዚአብሔር እጅ ያሉ የእግዚአብሔርን የእምነትና የወንድማማችነት መልእክት ወደ ዓለም ለመዘርጋት የሚያገልግሉ መሣሪያዎች ናቸው’፣ ስደትን የሚያቆም ማንም ስለሌለ በዚህ ንግደት ለዓለም ለመግለጥ የምንወደው ‘የስደት ጉዳይ በሕገ መንግሥት ብቻ የሚፈታ አለመሆኑ ነው’። ስደተኞችን መርዳት ኣለብን፣ ቢያንስ እንዲቀብልዋቸው ማድረግ ኣለብን፣ ቤተ ክርስትያንም ትሁን መንግሥታት በዚህ ጉዳይ መወያየት አለባቸው። የስደተኞች ጉዳይ ዓለም ከተፈጥሮ ጀምሮ ከሰው ልጅ ጋር የሚጓዝ ችግር ነው፣ ስለዚህ ሁላችን አብረን ስደተኞችን እንዴት አድረግን መቀበል እንዳለብንና ለችግራቸው የሚሆን ዘላቂ መፍትሔ መሻት አለብን፣ የሰው ሕይወት ክቡር ስለሆን ባለበት ጥሩ ኑሮ ትምህርት የጤና እንክብካቤ ሥራ ቤት እንዲያገኙ መጣር አለብን” ሲሉ ለተጠይቁት ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.