2009-08-14 13:10:29

ህንድ፣ ኦሪሳ


በሕንድ ኦሪሳ ክልል በሂንዱ ሃይማኖት በየአመቱ የሚከበረው የጃንማስታሚ በአል ምክንያት በዚህ ክልል በተደጋጋሚ ለሚከሠተው ሃይማኖታዊ ውጥረት እና ለማህበራዊ ሁከት መንስኤ እንዳይሆን ለመቆጣጠር የክልሉ RealAudioMP3 የጸጥታ ህይሎች በገፍ እንደሚሰማሩ ለማወቅ ተችለዋል። ነሓሴ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የሂንዱ አክራሪያን ሃይማኖት መሪ ስዋሚ ላክስማናንዳ ሳራስዋቲ ቅትለት ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት ሳይኖራቸው በዚሁ ሃይማኖት አክራሪያን በክልሉ ተቀስቅሶ የነበረው ጸረ ክርስትያን አመጽ ያስከትለው ሰብአዊ ማኅበራዊ ሁከት የቅርቡ ትውስት መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚህ ክልል ጸረ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ወሉደ ክህነት የደናግል ማህበራት እና አለማውያን ምእመናን በጠቅላላ ጸረ ክርስትያን ዓመጽ በተደጋጋሚ የሚታይበት ክልል መሆኑ ለሞት የተዳረጉት ካህናት ዓለማውያን ምእመናን የወደሙት አቢያተ ክርስትያን ይመሰክረዋል። ይህ የሂንዱ ሃይማኖት በዓል በሌላው ረገድ በሰው እጅ የተገደሉት የሃይማኖቱ መሪ የአንደኛው ዓመት ዝክረ እረፍት የሚፈጸምበት ዕለት በመሆኑ ብዙ ጥንቃቄ እና ቁጥጥር የሚያሻው መሆኑ የክልሉ የፖሊስ ጽ/ቤት ማሳሰቡ ኤሺያን ኒውስ የዜና አገግልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.