2009-08-12 17:40:08

የር.ሊ.ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ አስተምህሮ በካስተልጋንዶልፎ ከተማ ከሚገኘው ሐዋርያዊ አዳራሽ ቅጥር ግቢ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ ሰጡ። ትምህርቱም እንደሚከተል ነበር።

“ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ እፊታችን ቅዳሜ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሠታ እናከብራለን፤ እንዲሁም ይህ ዓመት የካህን ዓመት በመሆኑ፣ አጋጣሚውን በመጠቀም በቅድስት ድንግል ማርያምና በካህናት ተልእኮ መሀከል ያለውን ግኑኝነት ለመግለጽ እወዳለሁ። ግኑኝነቱ ጥልቅ የሆነና በምሥጢረ ሥጋዌ ላይ የተመሠረተ ነው። እግዚአብሔር በልጁ ሰው ለመሆን በወሰነበት ግዜ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ተባባሪነትና እሺታ ያስፈልገው ነበር፤ ነጻ የሆነ የፍጡሩ እሺ ማለት ያስፈለገው ምክንያት እግዚአብሔር ነጻነታችን ስለሚጠብቅ ያልፈለግነውን ነገር ከነጻነታችን አንጻር ስለማያደርግ ነው። እጅግ ኣስደናቂ የሆነ ምሥጢር ተከሠተ። ሁሉንም በእጁ የያዘ እግዚአብሔር የፍጡሩ እግዚእትነ ማርያም ነጻ ምርጫና እሺታ ጥገኛ ሆኖ የድንግል ማርያምን መልስ ይጠብቃል ማለት ነው።

ቅዱስ በርናርዶስ የዚህ ታሪካዊና ኣስተናቂ ፍጻሜ፣ የሰው ልጅን ታሪክ የሚለውጥ ወሳኝ የእመቤታችን ድንግል ማርያም መልስ ሲገልጽ፦ እግዚአብሔር የእግዚእትነ ማርያምን መልስ ሲጠብቅ፣ የእግዚእትነ ማርያም እሺ ማለት የደኅንነት መክፈቻ በመሆን እግዚአብሔርን በሰው ታሪክ እንዲገባ ፈቀደለት፤ እግዚአብሔር ባህርየ ትስብእት ለብሶ እንድኛ ሰው እንዲሆን በር ከፈተለት፤ በዚህም ቅድስት ድንግል ማርያም በምሥጢረ ሥጋዌ ብሎም በስው ልጆች የደኅንነት ታሪክ ጥልቅ በሆነ መንገድ ተሳታፊ ሆነች።

የምሥጢረ ሥጋዌ የወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ምሥጢር ከመጀመርያው ራስን መሥዋዕት ለማድረግ ያለመ ነበር። በላቀውና በመጨረሻው የፍቅር መግለጫ በመስቀል ላይ ስለደኅንነታችን ራሱን መሥዋዕት ያደረገበት፣ የሕይወት እንጀራ በመሆን ለመላው ዓለም ሕይወቱን ሰጠ። ስለዚህ ምሥጢረ ሥጋዌና መሥዋዕት አብረው ነው የሚጓዙት፣ ምሥጢረ ክህነትም ይህንን መሥዋዕት እውን ያደርጋል። ድንግል ማርያም የዚህ ምሥጢር ዋነኛ ተዋናይ ሆና ትገኛለች።

የመስቀሉን ምሥጢር የተመለከትን እንደሆነ፣ ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት እንቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙሩ እመስቀሉ ሥር ቆመው ይመለክታል። ከሐዋርያ ዮሓንስ የምንረዳው እንደ ግለ ሰብ ከኢየሱስ ጋር የነበረው ፍቅር ብቻ ሳይሆን እንደ ነዋሪ ምልክት የሁሉም ሐዋርያትና የሰው ልጆች፣ በተለይም ‘ፍቁራነ እግዚእ’ ለሆኑት ጌታ በልዩ መንገድ የጠራቸውና የመረጣቸው ካህናት ምልክት ነው። ኢየሱስ ለእናቱ፣ ‘እነሆ ልጅሽ” በማለት የመጨረሻውን የኑዛዜ ቃል በመናገር እንደ ልጅዋ ሆኖ እንዲንከባከባት ያማጥናል። ለሚወደው ሐዋርያም ‘ይህችውልህ እናትህ’ በማለት ተመሳሳይ የኑዛዜ ቃል ይናገራል።

ቅዱስ ወንጌል ሐዋርያው ከዚያ ሰዓት ጅምሮ ወደ ቤቱ ወሰዳት ይለናል። ወደ ቤቱ ወሰዳት የሚለው የግሪክ አንቀጽ ሲተረጐም በሕይወት ውስጥ መሳተፍን መወሃሃድን ያመለክታል። በካህናትን በቅድስት ድንግል ማርያም ተልእኮ መሃከል ያለው ግኑኝነትም በዚህ የተመሠረተ ነው። መጀመርያ ካህናት የልጅዋ ኢየሱስ እንደርሴዎችና አምሳያ ስለሆኑ በእናትነትዋ ትቀባቸዋለች፣ በሌላ በኩል ደግሞ በወንጌል ምሥክርነት ተልእኮኦዋቸው ኢየሱስን ለዓለም መስበክና ማሳወቅ ሥራቸው በመሆኑ የምሥጢሩ ተሳታፊዎች ይሆናሉ።

ልክ እንደ ኢየኡስ ማንኛውም ካህን የዚህች ከፍተኛና ትሕት እናት የተወደደ ልጅ መሆኑን ማወቅ አለበት። 2ኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ ‘ካህናት እግዝእትነ ማርያምን እንደ ፍጽምት አብነታቸው መውሰድ እንዳለባቸው ይገልጻል። የሊቀ ካህናት የሆነ ክርስቶስ እናት የሐዋርያት ንግሥትና ካህናትን በተልእኮአቸው የምትረዳ እናት ለምኚልን’ እያሉ ይለምንዋት ይላል። ጉባኤው ትምህርቱን በማያያዝ ‘ካህናት እግዚእትነ ማርያምን በእናታዊ ፍቅር እንዲያከብርዋትና እንዲያፈቅርዋት አደራ ይላል’።

የአርስ ቆሞስ የንበረ ቅዱስ ዮሐንስ ማርያ ቫያኒ፦ ‘ኢየኡስ ሁሉን ሰጥቶን ሲያበቃ በመጨረሻ የእርሱ ወንድማሞች እንድንሆን ዘንድ የላቀውን ውርሻ እናቱ ሰጠን ይላል’። ይህ ለሁሉም ክርስትያን ቢሆንም በተለይ ግን ለካህናት ይመለከታል።

ካህናት እውነተኛ የኢይሱስ ክርስቶስ መልክ በመልበስ በግዜአችን ባለው ችግር ሳይሸነፉ ኢየሱስን ለሁሉ ሰብከው እንዲችሉ ጸጋ ትሰጣቸው ዘንድ ማርያምን እንለምናት፣ የካህናት እናት የሆንሽ ድንግል ማርያም ለምኝልን እንበላት፣ ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.